በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕን ችሎት በመናቅ ተወነጀሉ


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የተከሰሱበትን የወንጀል ጉዳይ በማየት ላይ የሚገኘው የኒውዮርክ ችሎት ዳኛ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምስክሮች የሚሰነዝሩትን ነቀፌታ እንዲያቆሙ የሚያዘውን የዳኛ ትእዛዝ በመጣሳቸው ዛሬ ማክሰኞ የ9,000 ዶላር መቀጮ በየኑባቸው።

የኒውዮርክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሁዋን ሜርካን፤ በችሎት ሂደቱ ቁልፍ ምስክር ሆነው ሊቀርቡ በሚችሉ ሁለት ግለሰቦች ላይ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ተላልፈው ፈጽመዋል በሚል የቀረባበችውን ክስ ‘ለተነጣጠረብኝ የፖለቲካ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ስል ያደረግኩት ነው’ ሲሉ ተከሳሹ 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርገዋል። የትራምፕ ነቀፌታ እና ትችት ኢላማ የሆኑት ግለሰቦች የቀድሞ ጠበቃቸው የነበሩት ማይክል ኮኽን እና ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ፊልሞች ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልስ ናቸው።

ሜርካን የቀድሞው ፕሬዝደንት ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ደጋፊዎቻቸው የሰነዘሯቸውን አስተያየቶች መልሰው ማሰራጨታቸው የችሎቱን ትእዛዝ መጣስ እይደለም ሲሉ ትራምፕ ያቀረቡትን ይይግባኝ ጥያቄ "የማይገባ" ብለውታል። ዳኛው በተጨማሪም ትራምፕ በማሕበራዊ ሚዲያቸው ላይ ያወጡትን ጸያፍ ጽሁፍ እንዲያነሱ አዘዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG