በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሎባላይዜሽን - የአሜሪካና የቻይና የተለያዩ መንገዶች


የዩናይትድ ስቴትስና የቻይና ፕሬዚዳንቶች
የዩናይትድ ስቴትስና የቻይና ፕሬዚዳንቶች

የእሥያን የንግድ አቅጣጫ አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ለአካባቢው የንግድ መሪዎች ባደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ ጨርሶ የሚጣረሱ አመለካከቶችን አንፀባርቀዋል።

በቪየትሟ ሦስተኛ ግዙፍ ከተማ ዳ ናንግ የእሥያ-ፓሲፊክ አካባቢዎች ግዙፍ ኩባንያዎች ከፍተኛ መሪዎች በታደሙበት ስብሰባ ላይ ዛሬ የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በክልሉ ካለ ማንኛውም ሀገር ጋር የአንድ ለአንድ ውል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

“ከእኛ ጋር ለመሻረክ ከሚፈልግና የፍትሐዊና የጋራ እኩል ተጠቃሚነትን መርኅ ከሚያከብር ማንኛውም ኢንዶ-ፓሲፊክ ሃገር ጋር የሁለት ወገን የንግድ ስምምነቶችን እንፈጥራለን። ከእንግዲህ ወዲያ የማናደርገው ነገር እጆቻችንን በሚያስሩ፣ ሉዓላዊነታችንን አሳልፈን እንድንሰጥ በሚያደርጉና በተጨባጩ ትርጉም ባለው ማስፈፀም በማይቻሉ ግዙፍ ስምምነቶች ውስጥ አለመግባት ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ።

ትረምፕ አክለውም ባለፉ ሃገራቸው የንግድ መሰናክሎችን ዝቅ ባደረገችባቸው ጊዜዎች ሌሎች ሃገሮች የየራሳቸውን ገበያዎች ለዩናይትድ ስቴትስ ክፍት አላደረጉም ነበር ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

“ይሁን እንጂ - አሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ - ሸሪኮቻችን ከአሁን በኋላ ለደንቦች በታማኝነት ይገዛሉ ብለን እንጠብቃለን።”

በሌላ በኩል ግን ትረምፕን ተከትለው ወደ መድረኩ የዘለቁት ሃገራቸው መጠነ-ሰፊ በሆኑ መንግሥት-መር ዕቅዶች ግዙፍ እርምጃ እያደረገች ያለችው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሲ ጂንፒንግ የምጣኔ ኃብት ሁለንተናዊ ትስስርን /ግሎባላይዜሽን/ን ከእንግዲህ ለቀለበስ የማይችል ሂደት ነው ብለውታል።

ግሎባላይዜሽን - የአሜሪካና የቻይና የተለያዩ መንገዶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:33 0:00

ሚስተር ሲ በመቀጠል “በአሁኑ ጊዜ ለግሎባላይዜሽን የሚደረገው እርምጃ ከፊት ለፊቱ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚገፋው ንፋስ እየተገዳደረው ነው። ለዚህ ከምክንያቶቹ አንዱ በቂ በሆነ ሁኔታ አሣታፊ አለመሆኑ ሲሆን የተለያዩ ሃገሮችና በተለያዩ መስኮች ላይ ያሉ ሕዝቦች የልማትን ጥቅም እንዲያጣጥሙና በሩቅ ያለው ውብ ዕይታ እውን መሆኑን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጥረቶችን ማድረግ ይገባናል” ብለዋል።

የሁለቱ የዓለም ግዙፍ ምጣኔ ኃብቶችና የጦር ኃይሎች መሪዎች በዳ ናንግ መድረክ ላይ ያሰሟቸው ፊት ለፊት የሚጣረሱ መልዕክቶች ተፎካካሪ የሆኑት እነዚህ አመለካከቶች ዩናይትድ ስቴትስና ቻይናን መካከል ውለው አድረው ወደ ግጭት ይወስዱ ይሆን? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ ተሰምቷል - ወይስ በሰላም አብረው ለመዝለቅ ወደፊት መላ ይመቱ ይሆን?

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ግሎባላይዜሽን - የአሜሪካና የቻይና የተለያዩ መንገዶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG