ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስያ ጉብኝታችው ከተመለሱ በኋላ ቃል በገቡት መሠረት፣ ፍትህ የጎደለው የንግድ አሠራርዋ በሚሉት ምክንያት ቻይና ላይ ለመጠንከር መዘጋጀታቸውን ተንታኞች ይናገራሉ።
ፕሬዚዳንቱ ቻይናን በጎበኙበት ወቅት ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን የንግድ ግንኑነት ለራስዋ በሚጠቅም መንገድ በማራመድዋ “ይገባታል” ሲሉ መናገራቸው ሰዎችን ግራ አጋብቶ ነበር።
ፕሬዚዳንቱ በ $250 ቢልዮን ዶላር የሚገመት የንግድ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት “እኔ ቻይናን ጥፋተኛ አላደርግም። ለዜጎችዋ ጥቅም ሥልት ሌላን ሀገር በሚጠቅማት መንገድ ለመጠቀም የምትሞክር ሀገርን ማን ይነቅፋል? ሲሉ ተናግረው ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ “የአሜሪካውያንን የሥራ ዕድል፣ ሀብትንና የአእምሮ ንብረትን የሚዘርፍ አይነት ፍትህ የጎደለው የንግድ ሥራን በቸልታ ማያቱን አንቀጥልም ሲሉ በእስያ ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ባደረጉት ንግግርና ትላንት በዋይት ኃውስ ቤተመንግሥት ግልፅ አድርገዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ