በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ሥራቸውን ለቀቁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት የዶናልድ ትረምፕ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ቶም ቦሰርት ባልተጠበቀ ሁኔታ ዛሬ ማክሰኞ ሥራቸውን ለቀቁ፤ ሌሎች ሥራችውን ለመተው ከሚጠባበቁ ከፍተኛ የፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ እንደሆነም ታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት የዶናልድ ትረምፕ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ቶም ቦሰርት ባልተጠበቀ ሁኔታ ዛሬ ማክሰኞ ሥራቸውን ለቀቁ፤ ሌሎች ሥራችውን ለመተው ከሚጠባበቁ ከፍተኛ የፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ እንደሆነም ታውቋል።

ለቦሰርት ከሥራ መሰናበት የተሰጠ ኦፊሴላዊ ምክንያት አልቀረበም፣ ይሁንና ፕሬዚዳንቱ ለሦስተኛ ጊዜ የሀገር ደኅንነት አማካሪ አድርገው ያስቀመጧቸው ወግ አጥባቂው ጆን ቦልተን ወደ ሥልጣን በመጡ ማግሥት መሆኑ ነው የተሰናበቱት።

ብሉምበርግ የዜና አውታርም ሆነ ሲኤኔኤን እንደዘገቡት ከሆነ ግን፣ በቦልቶን ጥያቄ ነው ቦሰርት ሥራቸውን የለቀቁት።

የአርባ ሦስት ዓመቱ ቦሰርት ትራምፕ በትረ መንግሥቱን ከጨበጡበት ጊዜ አንስቶ በዋይት ኃውስ አስተዳደር ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ያገለገሉና፣ በተለይም በኢንተርኔት ደኅንነት ውስጥ ቁልፍ ሥፍራ የነበራቸው ሲሆኑ፣ ባለፈው ዓመት በቴክሳስ በፖርቶሪኮ እና በቨርጂን ደሴቶች ለደረሰው ነፋስ የቀላቀቀ የኃይለኛ ዝናም ጥፋት፣ መንግሥቱን ወክለው መልስ ሲሰጡ የነበሩ መሆናቸው ይታወቃል።

ሽብርተኛነትን በተመለከተም የፕሬዚዳንት ትረምፕን አስተዳደር እየተወከሉ በተደጋጋሚ መግለጫ በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG