በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከሰሜን ኮርያ መሪ የሚገናኙበት ቀንና የሚወያዩበት ስፍራ ተለይቶ ታወቀ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ዐርብ እንዳስታወቁት፣ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የሚገናኙበት ቀንና የሚወያዩበት ስፍራ ተለይቶ ታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ዐርብ እንዳስታወቁት፣ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር የሚገናኙበት ቀንና የሚወያዩበት ስፍራ ተለይቶ ታወቀ።

ፕሬዚደንት ትረምፕ፣ ወደ ደቡባዊ ምዕራብ የዩናይትድ ስቴትሷ ከተማ ዳላስ ከማምራታቸው አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በተናገሩት ቃል “አሁን ቀኑንና ሥፍራውን አውቀናል” ብለው፣ “የዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ዝርዝር ወደፊት ይገለጣል” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ አክለውም፣ «ዋሺንግተንና ፕዮንግያንግ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ውይይት ተዘጋጅተዋል» ብለው፣ ሰሜን ኮሪያ ያገተቻቸውን የሦስት ኮሪያ አሜሪካውያንን ጉዳይ ጠቆም ለማድረግም፣ “ታጋቾችን አስመልክቶም ብዙ ነገሮችን አከናውነናል” ብለዋል።

ሁለቱ ታጋች ኮሪያ አሜሪካውያን ቶም ኪም እና ኪም ሃከ ሶንግ ፕዮንግያንግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መምህራን ሲሆኑ፣ በሥለላ ተወንጅሎ የታገተው ሦስተኛው ኪም ዶንች ደግሞ፣ ራሶን ከተማ ውስጥ ነው እአአ በጥቅምት 2015 በቁጥጥር ሥር የዋለው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG