በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይም መጽሔት ዶናልድ ትረምፕን የዓመቱ ሰው አድርጎ መረጠ


ታይም መጽሔት ዶናልድ ትረምፕን የዓመቱ ሰው አድርጎ መረጠ
ታይም መጽሔት ዶናልድ ትረምፕን የዓመቱ ሰው አድርጎ መረጠ

ታይም መጽሔት ዶናልድ ትረምፕን የዓመቱ ሰው አድርጎ መርጧል። መጽሔቱ ትረምፕን የዓመቱ ሰው ብሎ ሲመርጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ትረምፕ እ.አ.አ በ2016 በመጽሔቱ የዓመቱ ሰው ተብለው ነበር።

ትረምፕ የዓመቱ ሰው ተብለው መመረጣቸውን ተከትሎ የዛሬውን የኒው ዮርክ የአክሲዮን ገበያ የመክፈቻ ደወል ደውለዋል።

ትረምፕ ደውሉን ከመደወላቸው በፊት፣ ባደረጉት ንግግር የዓመቱ ሰው ሆነው መመረጣቸው ትልቅ ክብር መኾኑን ተናግረዋል።

ከአራት ዓመታት በፊት በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተሸነፉትና፣ ውጤቱንም ያልተቀበሉት ትረምፕ፣ ከአራት ዓመታት በኋላ ባለፈው ወር በተደረገው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ወሳኝ በኾነ ድምጽ አሸንፈዋል።

መጽሔቱ ትረምፕን መምረጡ፣ ከአራት ዓመታት በፊት የነበረውን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ውዝግብ ምክንያት ከደረሰባቸው ፖለቲካዊ መገለል ወጥተው ለምርጫ ድል ለመብቃታቸው ዕውቅናን የሰጠ መሆኑን አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG