በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚያደርሱትን ወረራ ዲምክራቶች እየመሩ ነው አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሜክሲኮ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያመሩትን በርካታ የማዕከላዊ አሜሪካ ፍልሰተኞች ቡድኖችን ካላቆመች በስተቀር ከሀገሪቱ ጋር የሚዋሰነውን ድንበሬን እዘጋለሁ ሲሉ ዝተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሜክሲኮ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያመሩትን በርካታ የማዕከላዊ አሜሪካ ፍልሰተኞች ቡድኖችን ካላቆመች በስተቀር ከሀገሪቱ ጋር የሚዋሰነውን ድንበሬን እዘጋለሁ ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ማለዳ ላይ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚያደርሱትን ወረራ ዲምክራቶች እየመሩ ነው ሲሉ ከሰዋል። አያይዘውም ሜክሲኮ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚደረገውን ወረራ ካላቆመች ለማዕከላዊ አሜሪካ ሀገሮች የሚሰውጠውን ገንዘብ ሁሉ አቆማልሁ ብለዋል።

ትረምፕ ዛቻውን ያሰሙት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የሁንዱራስ ተወላጅ ስደተኞች ዩናይትድ ስቴትስ እንገባለን በሚል ተስፋ በጓቴማላ በኩል ሜክሲኮ ከደረሱ በኋላ ነው። ፍልሰተኞቹ ከአካባቢያቸው የወጡት ድኅነትንና ግጭትን በመሸሽ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG