በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በማይደራደሩ ላይ ታሪፍ እንደሚጥሉ ትረምፕ ተናገሩ

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በትክክሉ በማይደራደሩ ሀገሮች ላይ ታሪፍ እንጥልባቸዋለን ሲሉ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አስጠነቀቁ። ለዓለምቀፍ ንግድ ችግሮች መድሃኒቱ ይሄ ነው ሲሉም ተናገረዋል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በትክክሉ በማይደራደሩ ሀገሮች ላይ ታሪፍ እንጥልባቸዋለን ሲሉ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አስጠነቀቁ። ለዓለምቀፍ ንግድ ችግሮች መድሃኒቱ ይሄ ነው ሲሉም ተናገረዋል።

“ታሪፍ ግሩም ነገር ነው ዩናይትድ ስቴትስን ሲበድል የኖረ ሀገር ወይ በፍትሃዊ መንገድ ይደራደራል አለበለዚያ ቀረጥ ይቀምሳል፣ አለቀ! እኛ የገንዘብ ከረጢት ሆነን ስንበዘበዝ ኖረናል። ሁሉ ነገር ይስተካከላል።” ሲሉ ፕሬዚደንቱ በትዊተር ፅፈዋል።

ሚስተር ትረምፕ ይህን ያሉት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ “አውሮፓ ለሚስተር ትረምፕ ዛቻ አትንበረከክም” ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

የአውሮፓ ኮሚሽን ኃላፊ ዣን ክሎድ ዩንከር የለየለት የንግድ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል ከፕሬዚደንት ትረምፕ ጋር ሊነጋገሩ ነገ ወደ ዋሽንግተን ይጓዛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG