በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የም/ቤት ተደራዳሪዎች ግንብ የመገንባት ሥምምነት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የምክር ቤት ተደራዳሪዎች በደቡባዊው የሀገሪቱ ድንበር ግንብ ለመገንባት የሚያስችል ሥምምነት ያቀርባሉ የሚለው ግምታቸው ከአምሳ ከመቶ ያነሰ መሆኑ ገልፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የምክር ቤት ተደራዳሪዎች በደቡባዊው የሀገሪቱ ድንበር ግንብ ለመገንባት የሚያስች ሥምምነት ያቀርባሉ የሚለው ግምታቸው ከአምሳ ከመቶ ያነሰ መሆኑ ገልፀዋል።

በሁለቱም የምክር ቤት ወገን ባለው የተደራዳሪዎች ቡድን “በጣም ጥሩ ሰዎች” አሉ። ነገር ግን ግንቡን ለመገንባት ካቀድኩት $5.7 ቢልዮን ዶላር ያነሰ ገንዘብ የምቀበል አይመስለኛም ሲሉ ትላንት ዎል ስትሪት ጆርናል ለተባለው ጋዜጣ ተናግረዋል።

ለግንቡ የሚያስፈልገው ገንዘብ ካልተመደበላቸው በስተቀር ሌላ የመንግሥት መስርያ ቤቶች መዘጋት ጉዳይ አማራጭ ነው ብለዋል። የምክልር ቤት ውሳኔ ሳያስፈልጋቸው ግንቡን ለመገንባት እንዲችሉ ብሄራው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሊያውጁ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። ዲሞክራቶች እንዲህ አይነቱን አዋጅ በፍርድ ቤት ሊከራከሩበት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG