ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በካናዳ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ አዲስ ቀረጥ እንደሚጣል ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ትላንት በዓለም ዙሪያ የአክሲዮን ገበያ ዋጋ አሽቆልቁሏል። ሆኖም ፕሬዝደንቱ በሜክሲኮ እና በካናዳ ላይ የተጣሉት ቀረጦች ለአንድ ወር እንደሚያዘገዩላቸው ይፋ ካደረጉ በኋላ የገበያው ዋጋ በተወሰነ ደረጃ አንሰራርቷል። በሌላ በኩል ከቻይና በሚገቡ ምርቶች እና ሸቀጦች ላይ የተጣለው ተጨማሪ ቀረጥ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል። ቻይና በበኩሏ ከዩናይትድ ስቴትስ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ እንደምትጥል አስታውቃለች።
አኒታ ፓወል ከኋይት ሐውስ ያጠናቀረችው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም