በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለትረምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ


የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ቀን እና ሰዐት የሚያሳይ ታይፔ፣ ታይዋን ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት በር ላይ የተለጠፈ
የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ቀን እና ሰዐት የሚያሳይ ታይፔ፣ ታይዋን ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት በር ላይ የተለጠፈ

የቻይና እና የታይዋን መሪዎች ለወደፊቱ ግንኙነቶች ጥንቃቄ ከተሞላበት ተስፋ ጋራ ፣ ትረምፕ የአሜሪካን ምርጫ በማሸነፋቸው የ”እንኳን ደስ ያለዎት” መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ "ሁለቱንም ሀገራት እና ሰፊውን ዓለም" ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲሱ ዘመን ተስማምተው ለመኖር የሚያስችላቸውን ትክክለኛውን መንገድ እንዲሹ አሳስበዋል፡፡

የቻይናው መሪ ሁለቱ ወገኖች “በመከባበር መርህ፣ አብሮ መኖርና መጠቃቀም ላይ የተመሠረተ ግንኙነቶችን ለማስፋት ውይይትና ግንኙነትን በማጠናከር ልዩነቶችን በአግባቡ እየፈቱ የጋራ ትብብርና ጥቅሞችን ማስፋት ይችላሉ የሚል ተስፋ” እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ባላፈው ግንቦት ወደ ሥልጣን የመጡት የታይዋን ፕሬዝዳንት ላ ቺንግ-ቴ ለረጅም ጊዜ የዘለቀው በጋራ እሴቶችን እና ፍላጎቶች ላይ የተመሠረተው የታይዋን እና ዩናይትድ ስቴትስ አጋርነት፣ ለክልላዊ መረጋጋት ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ እንደሚቀጥል እና ወደ ላቀው ብልጽግና እንደሚያመራ” ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በቻይና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ትረምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ሊጥሉ እንደሚችሉ በመገመት የንግድ ጦርነቱ በቻይና ኢኮኖሚ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል የተደባለቀ ስሜቶቻቸውን ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ የታይዋን ዜጎችም የትረምፕ የግብይት ዘይቤ፣ በተለይም ትረምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ስለታይዋን የተናገሩት እና የውጭውን ዓለም የማግለል ፖሊሲያቸው፣ አሜሪካ ለታይዋን የምትሰጠውን ድጋፍ ሊያዳክሙ ይችላሉ ብለው እንደሚጨነቁ ተመልክቷል፡፡

ትረምፕ ባለፈው ሀምሌ ከብሉምበርግ ጋራ ባደረጉት ቃለጠመይቅ ታይዋን ድጋፍ ለሚሰጣት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ እንድትከፍል የጠየቁ ሲሆን፣ የኮምፒውተር እና የስልክ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ቁልፍ የሆነውን የ“ቺፕ”ሥራዎችን መቶ መቶ ወስዳብናለች ብለዋል፡፡

ተንታኞች ታይዋን ጠንካራ የመከላከያ ቁርጠኝነት ካላሳየች የትረምፕ ተለዋዋጭ የፖሊሲ እና የማግለል ዝንባሌ የታይዋንን ደህንነት ሊያዛባ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የቻይና ተንታኞች የአሜሪካ እና የታይዋን ወታደራዊ ትብብር መጨመር በተለይም የጦር መሳሪያ ግዢ ውጥረቱን ሊያባብሰው ይችላል ብለው ይጨነቃሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG