ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በቀጣዮቹ ስድስት ቀናት ውስጥ በስምንት ክፍለ ግዛቶች የምርጫ ዘመቻ የማካሄድ ዕቅድ ይዘዋል። በመጪው ማክሰኞ በሚካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ሪፖሊካውያን እንዲመረጡ ለማጣር አሥራ አንድ የፖለቲካ ስብስቦች ያካሄዳሉ።
ትረምፕ ዘመቻቸውን የፍሎሪዳ አስተዳዳሪ ሪክ ስካት ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት የሚያካሄዱትን ውድድር በመደገፍ በኢስቴሮ ፍሎሪድ ይጀመራሉ። የሚወዳደሩት ከዲሞክራቱ ሴኔተር ቢል ኔልሰን ጋር ነው። የምክር ቤት አባል ሮን ዴሳንቲስ ደግሞ ከዲሞክራቱ አንድሪው ጊለም ጋር ይወዳደራሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ