በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር


እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሃገራቸውን ከማንም በፊት እንደሚያስቀድሙ ሚስተር ዶናልድ ትረምፕ በድጋሚ አረጋገጡ።

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሃገራቸውን ከማንም በፊት እንደሚያስቀድሙ ሚስተር ዶናልድ ትረምፕ በድጋሚ አረጋገጡ።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 72ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ባደረጉት ንግግር በሰሜን ኮሪያ፣ በኢራን፣ በኩባ፣ በቬኔዝዌላ ላይ የበረቱ የማስጠንቀቂያ ቃላትን ሠንዝረዋል።

የሰሜን ኮሪያን ፕሬዚዳንት በስማቸው ሳይሆን “ሮኬትማን (የሮኬቱ ሰውዬ)” ብለው የጠሩት ትረምፕ ለሃገራቸው ደኅንነት አስፈላጊ ከሆነ ሰሜን ኮሪያን “ሙሉ በሙሉ ሊደመስሱ” እንደሚችሉ ዝተዋል።

“እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ሃገራችንንም መላውን ዓለም ለመበጣጠስ መፍቀድ ስለማንችል ልናቆመው ይገባል” ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በአንዳንድ ተግባሮቹ አሞግሰው ሙሉ አቅሙን ግን ማንቀሳቀስ አለመቻሉን በመግለፅ ወቅሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ።

ለመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:46 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG