በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትረምፕ አስተያየቶች ሳቢያ የደቡብ ኮሪያ ኑክሌር የመታጠቅ ጥያቄ እንደ አዲስ እያነጋገረ ነው


የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በዜና ፕሮግራም ላይ የሚያሳየውን የቲቪ ስክሪን በሴኦል የባቡር ጣቢያ እየተመለከቱ ደቡብ ኮሪያ እ አ አ ታኅሣስ 31/2019
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በዜና ፕሮግራም ላይ የሚያሳየውን የቲቪ ስክሪን በሴኦል የባቡር ጣቢያ እየተመለከቱ ደቡብ ኮሪያ እ አ አ ታኅሣስ 31/2019

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ሥልጣን ሊመለሱ ይችላሉ በሚል የደቡብ ኮሪያ ኑክሌር የመታጠቅ ጥያቄ እንደገና በማነጋገር ላይ ነው።

ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ሳምንት ከታይም መጽሔት ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሰጡትን አስተያየት፣ የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካ ወታደሮችን ከሃገሪቱ የማስወጣት ዛቻ አድርገው ተርጉመውታል።

ትረምፕ፣ በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች “አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። ኑክሌር ታጣቂዎን ጎረቤት ሰሜን ኮሪያን ለማመልከት ነው ተብሏል። በመሆኑም ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ለሚደረግላት ጥበቃ ተጨማሪ ክፍያ ማፈጸም አለባት ብለዋል።

“አንዲትን ባለጸጋ ሃገር ለምን እንጠብቃለን?” ያሉት ትረምፖ፣ “የአሜሪካ ወታደሮች መገኘት በሌለባችው ሌሎችም ሥፍራዎች ይገኛሉ” ብለዋል።

ትረምፕ ይህን መሳይ ንግግር ሲያደርጉ የመጀመሪያው አይደለም። በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ጥቅምና አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል።

የትረምፕ ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት አስትያየቶች 28 ሺሕ 500 የአሜሪካ ወታደሮች የሚገኙባት ደቡብ ኮሪያ፣ ወጪያቸውን በተመለከተ ተጨማሪ እንድትከፍል ለማድረግ የመደራደሪያ ስልት ነው። በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ወግ አጥባቂ ጋዜጦች የሃገሪቱ የኑክሌር ኃይል የመታጠቅን ጥያቄ እያነሱ በመጻፍ ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG