በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በፖሊሶች አያያዝ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚስችል ትዕዛዝ ፈረሙ


የዩናይትድ ስቴትስ ፐረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፐረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ዩናይትድ ስቴተስ ውስጥ ፖሊሶች ጭካኔ የተመላበት፣ የማጥቃት ተግባር ይፈፅማሉ በሚል፣ ቁጣ አዘል ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ለሳምንታት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን፣ የሃገሪቱ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በፖሊሶች አያያዝ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚያስችል ትዕዛዝ ትናንት ፈርመዋል።

ዲሚክራቶችና ሪፑብሊካውያን የምክር ቤት አባላትም በየበኩላቸው፣ በፖሊስ ሃይሉ አሰራር ላይ፣ ለውጥ ለማምጣት ጥረት እያደረጉ ናቸው።

ፐረዚዳንት ትረምፕ ትናንት በፖሊሶች ተከበው፣ በፖሊሶች አያያዝ ላይ አዲስ ትዕዛዝ ፈርመዋል። “የመጥፎ ፖሊሶች ቁጠር ኢምንት ነው ካሉ በኋላ፣ የጥሩ ፖሊሶችን ተግባር የማያጎድፍ አይነት ለውጥ እንዲደረግ ያሉትን ጥሪ አቅርበዋል።

የፖሊስ ኃይሉ ባጀት ማኅበራዊ አገልግሎት ወደሚሰጡ፣ ፖሊስ አልባ የህዝብ ደኅንነት ጥበቃ ተቋማት እንዲመደብ የቀረቡትን ጥሪዎች ግን፣ ፕረዚዳንቱ አልተቀበሉም።

ትረምፕ የፈረሙት በፖሊስ ኃይል አሰራር ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚያዘው መመሪያ፣ የፖሊስ ኃይል ክፍሎን ብቃት ማረጋገጥ፣ ከሚገባው በላይ ኃይል የመጠቀም ባህሪ ያላቸው ፖሊሶችን፣ ለመከታተል በሚያስችል መልኩ፣ መረጃ የመለዋወጥ ተግባርን ማጠናከር፣ የአእምሮ መታወክ፣

የአደንዛዥ እጽ ሱሰኝነትና ቤት አልባነት የመሰሉትን ችግሮች የሚከታትሉ አገልግሎቶችን መፍጠር የሚሉት ይገኙባቸዋል።

XS
SM
MD
LG