በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት በዩናይትድ ስቴትስ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ሃገራቸው እስከ መጪው ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት ይኖራታል ሲሉ ትናንት ማታ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት፣ የሪፖብሊካዊውን ፓርቲ ወክለው፣ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር የተሰጣቸውን ስያሜ በኦፊሴል ሲቀበሉ፣ ለሪፖብሊካውያኑ ጉባኤው ባደረጉት ንግግር ነው።

ጠበብት እንደሚሉት አስተማማኝነታቸው የተጠበቀና የተፈተኑ ክትባቶችን ለመስራት፣ የአሥርት ዓመታት ያህል ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ። ነገር ግን የኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር ሲባል፣ ክትባት ለመስራት በሚደረገው፣ ዓለምቀፍ ርብርብ መሰረት፣ በመጪው ዓመት አስተማማኝ የክትባት መድሃኒት ለማግኘት ይቻል ይሆናል የሚል ተስፋ አለ።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 5.8 ሚልዮን የሚሆኑ፣ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንዳሉ፣ ይህም በዓለም ደረጃ ካሉት ከ24 ሚልዮን በላይ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች፣ አንድ አምስተኛ እንደሚሆን፣ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG