በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ፑቲን ጠላቴም ወዳጄም አይደሉም አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሩስያው አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ጠላቴም ወዳጄም አይደሉም ብለዋል። በመጪው ሰኞ ሄልሲንኪ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ይታወቃል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሩስያው አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ጠላቴም ወዳጄም አይደሉም ብለዋል። በመጪው ሰኞ ሄልሲንኪ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ይታወቃል።

“ጠላቴም ወዳጄም አይደሉም በሚገባ አላውቃቸውም ሁለቴ ተገናኝተን በተነጋገርንበት ወቅት ግን በጥሩ ተግባብተናል” ሲሉ ዛሬ ብራሰልስ በሚካሄደው የሰሜን አተልንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት ጉባኤ ጎን ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ተናግረዋል።

ትረምፕ አያይዘውም ፑቲን ተፎካካሪ ናቸው። ወዳጅ ሊሆኑ የሚችሉበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን በሚገባ አላውቃቸውም” ብለዋል።

ትረምፕ ከፑቲን ጋር ሲገናኙ ስለ ስትራቴጃዊ የመሳርያ ቅነሳ ውል፣ ሩስያ የመካከለኛው ርቀት የኑክሌር ኃይሎች ውል ስለመጣስዋና ካች አምና ዩናይትድ ስቴስ በተካሄደው ምርጫ ላይ ጣልቃ ስለመግባትዋ ጉዳይ አነሳለሁ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG