በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስለ ፖርቶ ሪኮ


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

እጅግ ጠንካራ በሆኑ ተደራራቢ የውቅያኖስ ማዕበሎች ለተመታችውና የከበደ ጥፋት ለደረሰባት የካሪቤአኗ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ፖርቶ ሪኮ ፌደራሉ መንግሥት የተፋጠነ እርዳታ አቅርቧል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የአስተዳደራቸው አባላት እየተናገሩ ናቸው።

ለደረሰባት የካሪቤአኗ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ፖርቶ ሪኮ ፌደራሉ መንግሥት የተፋጠነ እርዳታ አቅርቧል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የአስተዳደራቸው አባላት እየተናገሩ ናቸው።

በአጥፊዎቹ የሐሩር አውራጃ ማዕበሎች በተለይ በኸሪኬን ማሪያ የተመቱት ፖርቶ ሪኮና እንዲሁም ቨርጂን ደሴቶች በከባድ ሁኔታ መውደማቸውንና መንግሥቱም በሁለቱም ግዛቶች ውስጥ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት አቅማቸውን የሚችለውን ሁሉ እያደረጉ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ተናግረዋል።

አስተዳደራቸውና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴና ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

በሌላ በኩል ግን በእነዚህ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት አካል በሆኑ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ዜጎቻቸው የፌደራሉ መንግሥት ጣልቃገብነትና እርዳታ አዝግሞብናል እያሉ ቅሬታ እያሰሙ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ የትናንት መልዕክታቸውን ያሰሙት ለዚያ አቤቱታ ምላሽ ለመስጠት ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት አልገለፁም።

ትረምፕ ፖርቶ ሪኮንና ቨርጂን ደሴቶችን የፊታችን ማክሰኞ እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በሺሆች የሚቆጠሩ ፌደራል ሠራተኞች ደሴቶቹ ላይ ተሠማርተው የአፋጣኝ እርዳታና ማገገሚያ ሥራ ቀን ተሌት ሳያቋርጡ እያከናወኑ መሆናቸውን የሃገር ውስጥ ጉዳዮች መሥሪያ ቤቱ ተጠባባቂ ሚኒስትር ኤሌይን ዱክ አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG