በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የ2016 የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ በተመለከተ ፑቲንን እጠይቃለሁ አሉ

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ በ2016 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጃቸው በእርግጥ ስለመኖሩ በአፅንዖት እንደሚጠይቋቸው፣ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ በ2016 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጃቸው በእርግጥ ስለመኖሩ በአፅንዖት እንደሚጠይቋቸው፣ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።

ሩስያ፣ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጇ የመኖሩ ወይም ያለመኖሩ ጥያቄ፣ ፌዴራላዊ ምርመራ እንዳስከተለ ይታወቃል።

ትራምፕ፣ ከብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጋር ከተገናኙ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ “ይህ ነገር ሀገራችንን በከፍተኛ ደረጃ ጎድቷታል” ማለታቸው ተጠቅሷል።

“ከሩስያ ጋር ያለን ግንኙነትም ተጎድቷል” ያሉት ፕሬዚዳንት ትረምፕ፣ “ተስፋ አደርጋለሁ፣ ይህን ጉዳይ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር እንፈታዋለን” ሲሉም ተደምጠዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG