የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት ማቀዳቸውን አስታወቁ።
ለአውሮፓውያኑ 2025 ዋዜማ ፍሎሪዳ በሚገኘው ማር-አ-ላርጎ ውስጥ በአዘጋጁት የዋዜማ ድግስ ላይ በቀብር ሥነ ስርዐቱ ላይ ይገኙ እንደሆነ ጥያቄ ለቀረበላቸው ጥያቄ "እገኛለሁ" ሲሉ ምላሽ የሰጡት ትራምፕ፣ በጉዳዩ ላይ ከካርተር ቤተሰብ ጋራ ተነጋግረው እንደሆነ ግን መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
ትራምፕ በኅዳር ወር ለተካሄደው ምርጫ ባደረጉት ዘመቻ በካርተር ላይ ጠንካራ ትችቶች ይሰነዝሩ የነበረ ሲሆን፣ በተለይ እ.አ.አ በ1970ዎቹ በነበረውን የዋጋ ንረት ምክንያት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ከካርተር ጋራ አወዳድረዋቸዋል።
ካርተር በ100 ዓመታቸው ባለፈው እሑድ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ግን ተመራጩ ፕሬዝዳንት በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው፣ "በፍልስፍናም ኾነ በፖለቲካው ከእርሳቸው ጋራ ባልስማማም፣ ሀገራችንን በእውነት ሀገራቸውን እንደሚወዱ እና እንደሚያከብሩ እገነዘባለሁ" የሚል መልዕክት አስፍረዋል። አክለውም "አሜሪካን የተሻለች ሀገር ለማድረግ ጠንክረው ሠርተዋል ለዚህም ከፍተኛ ክብር እሰጣቸዋለሁ" ብለዋል።
መድረክ / ፎረም