በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሕገ ወጥ ስደተኞች የሚወለዱ ሕፃናት ዜግነት እንዳይሰጣቸው የሚያዘውን የትረምፕ ደንብ የፌዴራል ዳኛ ለጊዜው አገዱ


ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጀንዋሪ 20 ቀን 2025 ዓ.ም በዋይት ሃውስ ኦቫል ኦፊስ የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ሲፈርሙ።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጀንዋሪ 20 ቀን 2025 ዓ.ም በዋይት ሃውስ ኦቫል ኦፊስ የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ሲፈርሙ።

በአሜሪካ ከሕገ ወጥ ስደተኞች የሚወለዱ ሕፃናት ዜግነት እንዳይሰጣቸው የሚያዘው የፕሬዝደንት ትርምፕ አዲስ ደንብ በፍርድ ቤት የመጀመሪያው ፈተና ገጥሞታል።

በሲያትል ዋሽንግተን በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ላይ የመንግስት ተወካይ የሆኑት ጠበቃ ክርክራቸውን ገና ከመጀመራቸው ነበር የፌዴራል ዳኛው ጃን ሲ ካፍኖር ጠበቃውን በጥያቄ አጣድፈው፣ የፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ “ግልጽ የሆነ የሕገ መንግሥት ጥሰት ነው” ያሉት፡፡

ዳኛው ቀጣይ ክርክር እስኪደረግ ድረስ የፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ ተፈጻሚ እንዳይሆን ለጊዜው አግደዋል።

በአሜሪካ በ14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሠረት በሃገሪቱ የተወለደ ሕፃን ዜግነት ያገኛል። ማሻሻው የወጣው የአሜሪካን የእርስ በእርስ ጦርነት ተከትሎ በእ.አ.አ 1868 ሲሆን፣ ይህም በወቅቱ ከባርነት ነጻ የወጡ ጥቁሮችን ዜግነት ለመስጠት ነበር።

ትረምፕ ሕገ ወጥ ስደተኞች እንዲባረሩ ትዕዛዝ የሰጡት ቃለ መሃላ በፈጸሙበት ባለፈው ሰኞ ነበር።

በመወለድ ዜግነት መሰጠቱን የሚቃወሙ ወገኖች፣ አጋጣሚው ሕገ ወጥ ስደተኞች በሃገሪቱ እንዲቆዩና ልጆቻቸው መልሰው ዜጋ እንዲያደርጓችው መንገድ የሚከፍት እንደሆነ ይሟገታሉ።

የትላንቱ የዳኛው ውሳኔ በመላው ሃገሪቱ የትረምፕ ትዕዛዝን ተፈጻሚነት ለ14 ቀናት የሚያግድ ነው።

ዳኛው ለእ.አ.አ የካቲት 6 ቀን 2025 ቀጠሮ የሰጡ ሲሆን፣ እስከዛው ተከራካሪ ወገኖች በፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ ላይ ያላቸውን ሕጋዊ ሙግት ያቀርባሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG