በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የመርዛም ዛፍ ፍሬ" - ናንሲ ፔለሲ

ባለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ውስጥ ሩሲያ ጣልቃ መግባት አለመግባቷን እያጣሩ ያሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ቁልፍ እንደራሴዎች የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የበኩር ልጅ ዶናልድ ትረምፕ (ጁኒየር) ቃል እንዲሰጡ እየጠየቁ ነው፡፡

ባለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ውስጥ ሩሲያ ጣልቃ መግባት አለመግባቷን እያጣሩ ያሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ቁልፍ እንደራሴዎች የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የበኩር ልጅ ዶናልድ ትረምፕ (ጁኒየር) ቃል እንዲሰጡ እየጠየቁ ነው፡፡

ዶናልድ ትረምፕ (ጁኒየር) ከአሁኑ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት፤ ከያኔ ዕጩ ፕሬዚዳንት አባታቸው የዘመቻ ጉዳይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከአንዲት የሩስያ የሕግ ባለሙያ ጋር ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው ትረምፕ ሰማይ-ጠቀስ ሕንፃ ውስጥ ባለፈው ዓመት ተገናኝተው የመወያየታቸው ጉዳይ በሰሞኑ የአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የተጋጋለ ንግግር አስነስቷል፡፡

የሩሲያ አቃቤ ሕግ መሆናቸውና ከክረምሊን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ዘግይቶ ግን ከመንግሥቱ ጋር ግንኑነት እንደሌላቸው ከተሰማው የሕግ ሰው ጋር ዶናልድ ትረምፕ (ጁኒየር) በተገናኙበት ወቅት የአባታቸውን ዘመቻ ሊጠቅም፤ በአንፃሩ ደግሞ ተፎካካሪያቸው የነበሩትን የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ዕጩ ሂላሪ ክሊንተንን ሊጎዳ ይችላል የተባለ መረጃ መለዋወጣቸው ነው በስፋት የሚናፈሰው፡፡

የቪኦኤው ጂም መሎን ከዋሺንግተን ተጨማሪ ዘገባ ልኳል፡፡

"የመርዛም ዛፍ ፍሬ" - ናንሲ ፔለሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG