በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ትረምፕ የህግ መምርያው ም/ቤት ውሳኔ ንፁህነቴን አረጋጧል አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የህግ መምርያው ምክር ቤት ውሳኔ ንፁህነቴን አረጋጧል እያሉ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የህግ መምርያው ምክር ቤት ውሳኔ ንፁህነቴን አረጋጧል እያሉ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምርያ ምክር ቤት የሥለላ ኮሚቴ ሲያካሄድ በቆየው ምርመራ ባለፈው ዓመት በተደረገው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ሩስያ በአሜሪካ የፖለቲካ ተቋማት ላይ የሳይበር ጥቃት አድርሳለች። ነገር ግን የትረምፕ የምርጫ ዘመቻ ትብብር አልነበረበትም የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ትላንት አስታውቋል።

ትረምፕ ደስታቸውን በትዊተር ገልፀውል። ዲሞክራቶች ግን በሪፖብሊካውያን የሚመራው መርመሪ ኮሚቴ ከባድ የምርመራ ሂደት ባለማድረጉ ለዩናይትድ ስቴትስ ለመከላከል አልቻለም ሲሉ ነቅፈዋል።

በህግ መምርያው ምክር ቤት የዲሞክራት አባላት መሪ ናንሲ ፔሎሲ ይህ የምክር ቤቱ ሪፖብሊካውያን አባላት በሩስያ ተግባር ላይ የሚደረገውን ምርመር “ለማሰናክል” የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው ሲሉ ነቅፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG