በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ለፍሊን ምህረት ይሰጡ ይሆን?

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የአስተዳደራቸው የፀጥታ አማካሪ ሆነው ሦስት ወር ለሚሆን ጊዜ ካገለገሉ በኋላ ለተባረሩት ማይክ ፍሊን ምህረት የመስጠት አለመስጠታቸውን ጉዳይ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ክፍት አደረጉ።

የአስተዳደራቸው የፀጥታ አማካሪ ሆነው ሦስት ወር ለሚሆን ጊዜ ካገለገሉ በኋላ ለተባረሩት ማይክ ፍሊን ምህረት የመስጠት አለመስጠታቸውን ጉዳይ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ክፍት አደረጉ።

ጄነራል ፍሊን ከዋይት ሃውስ አማካሪነታቸው የተባረሩት ቀደም ሲል ዋሺንግተን ከነበሩት የሩሲያ አምባሣደር ጋር የነበሯቸውን ግንኙነቶች አስመልክቶ ለፌደራሉ የምርመራ ቢሮና ለምክትል ፕሬዚዳንቱ ዋሽተዋል ተብለው ነበር።

“አሁን ለጊዜው ስለ ማይክል ፍሊን ይቅርታ ጉዳይ መናገር አልፈልግም” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዛሬ ለኤፍቢአይ ብሔራዊ አካደሚ ንግግር ለማድረግ ከቤተመንግሥቱ ከመነሣታቸው በፊት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ምን እንደሚሆን እናያለን። ኤፍቢአይ እና ፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ እየተከናወነውን የሚያይ ሰው በጣም ተናድዷል” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG