በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ “በምርጫው ከተሸነፍኩ ተጭበርብራል″ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል


ፕሬዘዳንት ኦባማ ትራምፕ የአሜሪካ የምርጫ ሂደት የተጭበረበረ ነው ማለታቸውን ነቀፉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ለፕሬዘዳንትነት የሚወዳደሩት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ″በመጪው ወር በሚካሄደው ምርጫ ከተሸነፍኩ የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል ማለት ነው″ ማለታቸውን ነቅፈዋል።

ትራምፕ የሩስያውን ፕሬዘዳንት ቭላዲሚር ፑቲንን ማድነቃቸውንም ከዚህ ቀደም ያልተደረገ ሲሉ ነቅፈዋል።

ፕሬዘዳንት ኦባማ ይህን ያሉት ትላንት ዩናይትድ ስቴትስን ከጎበኙት የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማተዎ ረንዚ ጋር ሆነው ባካሄዱት ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ነው።

የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ

የኢጣልያ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቲዮ ሬንዚ ትናንት በሃይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ኦፊሴላዊ የምሳ ግብዣ ከተደረገላቸው በኋላ የደመቀ የእራት ግብዣም ተደርጎላቸዋል፡፡

በፕሬዘደንት ኦባማ የተደረገ መጨረሻው መንግስታዊ የእራት ግብዣ ይሆናል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ዘጋቢ ዝላቲካ ሆክ ያጠንቀረችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

ትራምፕ በምርጫው ከተሸነፉ ተጭበርብራል ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

XS
SM
MD
LG