በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የዩክሬኑን ጦርነት ማስወገድ ይቻል እንደነበር በሚገልጹት ላይ እንደሚስማሙ ፑቲን  አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

ዶናልድ ትረምፕ፣ እርሳቸው በሥልጣን ላይ ቢሆኑ ኖሮ የዩክሬኑን ጦርነት ማስወገድ ይቻል ነበር ሲሉ በተደጋጋሚ በሚገልጹት ላይ እንደሚስማሙ የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን አስታውቀዋል።

ሞስኮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ጋራ መወያየት እንደምትሻም ፑቲን አስታውቀዋል። ፑቲን ዛሬ ከሩሲያ መንግሥት ቴሌቪዥን ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ትረምፕ ለአሜሪካ በሚጠቅማት ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ “ብልህና የተግባር ሰው” ናችው ሲሉ ገልፀው፣ ከዩክሬኑ ግጭት በተጨማሪ፣ የኑክሌር ጦር መሣሪያ ቁጥጥር እና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተም መወያየት እንደሚሹ አስታውቀዋል።

“ከትረምፕ ጋራ ሁሌም ሥራ ላይ ያተኮረ፣ ተግባራዊ እና መተማመን የሰፈነበት ግንኙነት አለን” ሲሉ አክለዋል ፑቲን። “በወቅቱ ፕሬዝደንት ቢሆኑ ኖሮና ምርጫው ባይሰረቅ፣ በዩክሬን የተከሰተውን ግጭት ማስወገድ ይቻል ነበር ሲሉ ትረምፕ በሚናገሩት አለመስማማት አልችልም” ሲሉ ተደምጠዋል ፑቲን።

የፑቲን መግለጫ ትረምፕ የ2020ውን ምርጫ ተሰርቂያለሁ ብለው በሚከራከሩት ላይ የተሰጠ ጠንካራ ድጋፍ ነው ተብሏል።

ትረምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋራ ትላንት ሐሙስ ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ግጭቱን ለማስወገድ ከፑቲን ጋራ መደራደር እንደነበረባቸው ተናግረዋል።

ፑቲን በዛሬው መግለጫቸው ለንግግር በራቸው ክፍት መሆኑን አስታውቀው፣ ነገር ግን ዜሌንስኪ በእ.አ.አ 2022 ከሞስኮ ጋራ ድርድር እንደማይኖር መወስናቸውን አንስተው አስታውሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG