በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን፣ ቪየትናም ውስጥ በሚካሄደው የእስያ ፓሲፊክ ሀገሮች የኢኮኖሚ ጉባዔ ወቅት የጎንዮሽ ንግግር ያደርጉ ይሆናል የተባለውን ግምት ዋይት ሃውስ “የለም” አለ።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩስያው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን፣ ቪየትናም ውስጥ በሚካሄደው የእስያ ፓሲፊክ ሀገሮች የኢኮኖሚ ጉባዔ ወቅት የጎንዮሽ ንግግር ያደርጉ ይሆናል የተባለውን ግምት ዋይት ሃውስ “የለም” አለ።

ሁለቱም መሪዎች ጉባዔውን የሚሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል።

“ሲገናኙ ጥቂት የግል ጭውውት ሊኖር እንደሚችል ቢገመትም” አሉ የዋይት ሃውሷ ፅሕፈት ሚኒስትር ሳራ ሃከቤ ሳንደርስ

“ይህ ነው የሚባልና ሚዛን የሚደፋ ውይይት እንዳልሆነና በሁለቱ መሪዎች መካከል በፕሮግራም የተያዘ የጋራ ንግግር እንደማይኖር ነው ሳንደርስ የገለፁት።

የሩስያው ዜና አውታር /RIA Novosti/ በበኩሉ በዛሬ ዕለት እንደዘገበው ከሆነ ግን፣ የዋይት ሃውስን አባባል ይቃረናል።

“ሁለቱ መሪዎች እንዲህ በግላጭ ተገናኘተው ያለ አንዳች ውይይት አይለያዩም፣ ምናልባትም ውኃ ሊቋጥር የሚችል ውይይት ሊያካሂዱ ይችላሉ” ብሏል።

“ፑቲንና ትራምፕ በቪየትናሙ የDanang ጉባዔ ላይ ሊወያዩ የሚችሉበትን ሁኔታ ክሬምሊን እያመቻ ነው” ተብሎም በአንድ መጽሔት ላይ ተዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG