በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕና ፑቲን በሄሊሲንኪ


በፊንላንዷ ዋና ከተማ ሄሊሲንኪ ከሩስያው አቻቸው ጋር ቭላድሚር ፑቲን በያዙት በያዙት ጉባኤ ሞስኮ በአገራቸው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ “ጣልቃ ገብ ሥራ መሥራቷን” አስመልክቶ “ሠፊ ጊዜ ወስጄ አነጋገርኳቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ። ይሁን እንጂ ለዚህ ድርጊቷ ሩስያን በቀጥታ ያለመውቀሳቸው ተዘግቧል።

በአገራቸው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ “ጣልቃ ገብ ሥራ መሥራቷን” አስመልክቶ “ሠፊ ጊዜ ወስጄ አነጋገርኳቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ። ይሁን እንጂ ለዚህ ድርጊቷ ሩስያን በቀጥታ ያለመውቀሳቸው ተዘግቧል።

በፊንላንዷ ዋና ከተማ ሄሊሲንኪ ከሩስያው አቻቸው ጋር ቭላድሚር ፑቲን በያዙት ጉባኤ ሞስኮ በአገራቸው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ “ጣልቃ ገብ ሥራ መሥራቷን” አስመልክቶ “ሠፊ ጊዜ ወስጄ አነጋገርኳቸው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ። ይሁን እንጂ ለዚህ ድርጊቷ ሩስያን በቀጥታ ያለመውቀሳቸው ተዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ“በዛሬው ንግግራችን ወቅት ሩሲያ በአገራችን የምርጫ ሂደቶች ጣልቃ መግባቷን በተመለከተ በአካል ተገናኝቶ መናገርን የመሰለ እንደሌለ ነው የተሰማኝ” ብለዋል። ትራምፕ ይህን ያሉት ከንግግራቸው በሁዋላ ከሩሲያው መሪ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋማት ሩሲያ በ2016ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ መግባቷን ካረጋገጡበት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ይታወቃል። ይሁን እንጅ ፕሬዝዳንት ፑቲን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት በሰጡት አስተያየት “ሩስያ ፈጽሞ ጣልቃ ያለመግባቷን ደግሜ ልናገር። ወደፊትም በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ .. በአሜሪካ የምርጫ ሂደት ጣልቃ የመግባት ዕቅድ የላትም” ብለዋል።

የፑቲንን ምላሽ አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ትራምፕ በበኩላቸው፤ በዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋማት በእጅጉ እንደሚተማመ ተናግረው፤ “ነገር ግን ፑቲንም እጥብቀው ነው ያስተባበሉት” ሲሉ መልሰዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG