ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የሩስያው አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን የመጀመርያው ስብሰባቸውን ሄልሲንኪ ላይ እአአ ሀምሌ 16 ቀን፣ ከ19 ቀናት በኋላ ያደርጋሉ።
የጉባዔው ቀን በሁለቱም ሀገሮች የተረጋገጠ ሲሆን የትረምፕ ብሄራዊ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ለጉባኤው ለማመቻቸት ሲሉ ከሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲንና ከሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች ጋር ተገንኝተው በተነጋገሩ ማግሥት ነው ስለጉባኤው የተገለፀው።
ቦልተን ትላንት ሞስኮ ሆነው ለዓለምቀፍ ጋዜጣኞች በሰጡት መግለጫ በፕሬዚዳንት ትረምፕና በፕሬዚዳንት ፑትን መካከል ጉባዔ ለማካሄድ ይቻል እንድሆነ ከሩስያ ባለሥልጣኖች ጋር እንድነጋገር ትረምፕ ልከውኛል ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ