በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ስለጠመንጃ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠመንጃዎች የከፋ ጉዳት እንዲያደርሱ የሚያደርጉ መሳርያዎች እንዲታገዱና በጠመንጃ ገዢዎች ላይ ጥብቅ የታሪክ ጀርባ ምርመራ እንዲደረግ ምክረ ሀስብ አቅርበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠመንጃዎች የከፋ ጉዳት እንዲያደርሱ የሚያደርጉ መሳርያዎች እንዲታገዱና በጠመንጃ ገዢዎች ላይ ጥብቅ የታሪክ ጀርባ ምርመራ እንዲደረግ ምክረ ሀስብ አቅርበዋል። በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ አሜሪካ ውስጥ የተኩስ ሰለባ የሆኑት ተመሪዎች፣ አስተማሪዎችና ቤተሰቦች በዋይት ኃውስ ተሰባስበው የሚሉትን እያዳመጡ ነው።

በዋይት ኃውስ ከተሰባሰቡት ተማሪዎች መካከል ባለፈው ረቡዕ ተኩስ ተከፍቶበት 17 ተማሪዎች ከተገደሉበት ማርጀሪ ስቶንማን ዶግለስ ከተባለው በፓርክላንድ ፍሎሪዳ ከሚገኘው የሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤት የመጡ ይገኙባቸዋል። ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ደግሞ የመሳርያ ቁጥጥር እንዲደረግ በመጠየቅ በፍሎሪዳ ምክር ቤት ሰልፍ አካሄደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG