በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀጣዩ የትራምፕ ዕጣ በፖለቲካው ዓለም



የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ እኤአ ጥር 9 /2019፣ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ማይክ ፔንስን አስከትለው በምክር ቤቱ በተደረገ የፖሊሲ ውይትት ምሳ ላይ ከተገኙ በኋላ ፣ ከህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ መሪ ሚች መካኔል ጋር ለመሰነባበት ሲጨባበጡ
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ እኤአ ጥር 9 /2019፣ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ማይክ ፔንስን አስከትለው በምክር ቤቱ በተደረገ የፖሊሲ ውይትት ምሳ ላይ ከተገኙ በኋላ ፣ ከህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ መሪ ሚች መካኔል ጋር ለመሰነባበት ሲጨባበጡ

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሥልጣናቸው ቢነሱም ከፖለቲካው ዓለም አልወጡም፡፡ ትራምፕ በሪፐብሊካኖች ዘንድ አሁንም ዝነኛ ሲሆኑ፣ ፓርቲውን ለመቆጣጠር በሚደረገው ፍልሚያ ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግብግብ ይዘዋል፡፡

በትናንትናው እለት የትራምፕ ፕላዛ ሆቴልና ከሱም ጋር ተያይዞ በቁማር መጫወቻ ስፍራነቱ የሚታወቀው ዝነኛው ህንጻ ወይም ካሲኖ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ በኒው ጀርሲ ክፍለ ግዛት አትላንቲክ ሲቲ በሚባለው ቦታ የሚገኘው የቁማር ቤት ወይም ካሲኖ በአንድ ወቅት በቁማር መጫወቻ ስፍራዎች የበላይነት ያለውና ገናና ስፍራ ነበር፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ግን በፖለቲካው ዓለም ገና እጃቸውን አልሰጡም፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት የንዑሳን መሪና የሪፐብሊካን ፓርቲ ቁንጮ የሆኑትን ሚች መካነልን ወርፈዋቸዋል፡፡

መካኔል እኤአ ጥር 6 በምክርቤቱ ህንጻ ለተነሳው አመጽ ትራምፕ ተጠያቂ መሆናቸውን በመግለጽ የሚከተለውን ተናግረው ነበር

“ፕሬዚዳንት ትራምፕ በተግባርም ሆነ በስነምግባር አመጹን በማነሳሳት ተጠያቂነት አለባቸው፡፡”

ትራምፕ ባወጡት መግለጫ ሚች መካኔልም ሆኑ እሳቸውን የደገፏቸው የምክር ቤት አባላት፣ ካሁን በኋላ በድጋሚ አይመረጡም፡፡ እሳቸውም በየአካባቢው በሚደረገው የቀዳሚ ምርጫ፣ ኃላፊነት ላይ ያሉትን የሪፐብኪላን ፓርቲ አባላት የሚፎካከሩ የቀኝ አክራሪ የፓርቲ ዕጩዎችን እንደሚደግፉም አስጠንቅቀዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት የምርጫ ዘመቻ አማካሪ ጄሰን ሚለር የትራምፕን ሀሳብ አብራርተዋል

“ዋናው ግብ ለትራምፕ ድምጻቸውን ለሰጡት 75 ሚሊዮን አሜሪካውያን ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሁንም በፖለቲካው ውስጥ ያሉና ተሳታፊ መሆናቸውን መልክት ማስተላለፍ ነው፡፡ አሜሪካ ትቅደም የሚለውን አጀንዳ የሚያራምዱ እጩዎችን መደገፋቸውን የሚቀጥሉ መሆኑን መግለጽ ዋነኛው ግብ ነው፡:”

በቀድሞ ፕሬዚዳንት ላይ በተመሰረተው ክስ የጥፋተኝነት ውሳኔውን በመደገፍ ድምጻቸውን በሰጡት ሰባት የሪፐብሊካን የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት ላይ የቀረበውም ትችት ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በሰባቱ ላይ ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት የቀረበባቸው ግሰጻ በየአካባቢው ያሉ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕን ከመደገፍ የማይመለሱ መሆኑን የሚያመላክት ይመስላል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ ተጠያቂነት ፕሮጀክት ማዕከል ድሬክተር የሆኑት ኦሊቪያ ትሮየ ይህንኑ ሀሳብ ያጠናክራሉ፡፤

“የሪፐብሊካን ፓርቲ የትራምፕ ፓርቲ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ መርህ ያላቸው ወግ አጥባቂዎች፣ለምሳሌ እኔ በፖለቲካው ራሴን አድርጌ እንደምወስደው፣ እንደኔ ብዙም ወደ ቀኝ ያልሄዱ፣ በመሃል ያሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች መሄጃ ያጡ ፓርቲ አልባ ሰዎች ይመስሉኛል፡፡”

በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ በተነሳው አመጽ ትራምፕ ተጠያቂ ናቸው ብለው የሚያስቡት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ግን አሁንም ሁኔታውን ዝምብለው የሚለቁት አልመሰሉም፡፡ እኤአ መስከረም 11/ 2001 የተፈጠረውን የአሸባሪዎች ጥቃት ለመመርመር እንደተቋቋመው ኮሚሽን ለዚህኛውም ጥቃት ተመሳሳይ ገለልተኛ የሆነ የመርማሪ ኮሚሽን ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

የመስከረም አስራ አንዱ ጥቃት መርማሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር የነበሩት ቶማስ ኬን እኤአ ጥር 6 ለተፈጠረው ጥቃትም ተመሳሳይና ገለልተኛ የሆነ ተቋም እንዲመሰረት አሳስበዋል፡፡ ታዲያ ይላሉ ኬን

“ይህ ኮሚሽን መቋቋም ያለበት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለማግኘት አይደለም፡፡ ይህ ኮሚሽን እውነቱን የሚያፈላልግ ነው፡፡”

በቅርቡ የተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ድምጽ እንደሚያሳየው 75 ከመቶ የሆኑት ሪፐብሊካኖች በፓርቲያቸው ውስጥ ትቅል ድርሻ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፡፡ ትራምፕም ይህን ብለዋል

“እንወዳችኋለን! በሆነ አንድ መንገድ እንመለሳለን፡፡”

ይሁን እንጂ በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ የተፈጸመው ጥቃትና፣ በምርጫ ሂደት ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ በትራምፕ ላይ የሚካሄደው የወንጀል ምርመራ፣ እንዲሁም በታክስና በኢንሹራንስ ማጭበርበር ላይ የተነሱ የህግ ጥያቄዎች፣ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የወደፊት የፖለቲካ እጣ ላይ ወሳኝነት ይኖራቸዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡

(በቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ከላከችው ዘገባ የተወሰደ)

ቀጣዩ የትራምፕ ዕጣ በፖለቲካው ዓለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

XS
SM
MD
LG