በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ምርጫው በትክክል መከናወኑ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ገለፁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ መጪው ሃገርቀፍ ምርጫ በትክክል መከናወኑ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ መግለፃቸውን ቀጥለዋል።

በፖስታ ቤት በኩል የሚላክ የመራጭ ድምፅ ይጭበረበራል ብዬ እሰጋለሁ ያሉ ሲሆን ብዙዎች ባለሥልጣናት ደግሞ ያለአግባብ የተጋነን ስጋት ነው ብለው ይተቻሉ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዋይት ሃውስ ለሰሜን ካሮላይናና ፍሎሪዳ ጉዟዋቸው ከመነሳታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ምርጫው በትክክል መከናወኑን እንዲረጋገጥ እንፈልጋለን፤ መሆኑን ግን እንጃ ብለዋል።

“ብዙ የድምጽ መስጫ ካርዶች ወንዝ ውስጥ ተገኝተዋል፤ ትረምፕ የሚሉ ካርዶች ቁሻሻ ማጠራቀሚያ ተወርውረዋል” ብለዋል።

የፔንሲልቬንያ ክፍለ ግዛት የዩናይትድ ስቴትስ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ባለው መሰረት ከጦር ሰራዊት አባላት የተላኩ ጥቂት የድምፅ መስጫ ካርዶች ተጥለው ከመካከላቸው ዘጠኙ በፍለጋ ተገኝተዋል። ከዚያ ውስጥ ሰባቱ ለፕሬዚዳንት ትረምፕ የተሰጡ ድምፆች ያለው የፍትህ ሚኒስቴር ሁለቱ ማንን እንደመረጡ አልታወቀም ብለዋል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ካሊፎርኒያና ኮሎራዶን ጨመሮ በበርካታ ክፍለ ግዛቶች ለነዋሪዎች በሙሉ በፖስታ ቤት በኩል ድምፅ መስጫዎች እየተላከ መሆኑ አሳስቦኛል ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG