በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ ሹመት ፀደቀ


የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛነት ያጯቸውን ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረትን ሹመት ትናንት ሰኞ ፀደቀ።
የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛነት ያጯቸውን ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረትን ሹመት ትናንት ሰኞ ፀደቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛነት ያጯቸውን ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረትን ሹመት ትናንት ሰኞ አጽድቋል።

ሪፖብሊካኗ ሴኔተር ሱዛን ኮሊንስ ከመላው የመወሰኛው ዲሞክራት አባላት ጋር ሆነው የዳኛይቱን ሹመት ተቃውመው ድምፅ ሰጥተዋል።

የዳኛ ባረትን ሹመት መፅደቅ የተቃወሙት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው እጅግ በተቃረበበት ጊዜ የመጣ በመሆኑ እንደሆነ ሴነተር ኮሊንስ ገልጸዋል።

በአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባልፉት ቢያንስ አንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ በመወሰኛ ምክር ቤቱ አናሳ መቀመጫ ካለው ፓርቲ አንዳችም የድጋፍ ድምፅ ሳይሰጠው ሹመቱ የጸደቀለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኖሮ አያውቅም።

ዳኛ ባረት ሹመታቸው በመወሰኛ ምክር ቤቱ ከፀደቀ በኋላ በዋይት ሃውስ በተካሄደ ሥነ ስርዓት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ክላረንስ ቶማስ ቃለ መሃላ አስፈጽመዋቸዋል።

XS
SM
MD
LG