በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ሀገራቸው ከውጭ በሚገቡ የብረት፣ አሉሚኒየም ምርቶች ቀረጥ ውሳኔ እንደምትጸና ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው ከውጭ በሚገቡት የብረት ምርቶች 25 ከመቶ በአሉሚኒየም ምርቶች ደግሞ 10 ከመቶ ቀረጥ ለመጣል በወሰደችው ውሳኔ እንደምትጸና ትላንት ተናግረዋል። የፖለቲካና የዲፕሎማሲ አጋሮች እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች አሜሪካ የንግድ ጦርነት ሊያስከትል የሚችል ፖሊሲን እንዳትከተል ጫና እያደረጉ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትላንት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኒታንያሁ ጋር ተገናኝተው ከመነጋገራቸው በፊት አዲስ ፍትሃዊ የሆነ የሰሜን አሜሪካ የአጻ ንግድ ስምምነት ከተደረገ ሜክሲኮና ካናዳ ቀረጥ ከመጣሉ እቅድ ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

“ዋግ ቢስ የነበረውን የሰሜን አሜሪካ ነጻ የንግድ ስምምነትን ለማሻሻል እየተደራደርን ነው። ስምምነት ላይ ካልደረስን ግን አቆመዋለሁ” ሲሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዝተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሜክሲኮና ካናዳ የሰሜን አሜሪካ ነጻ የንግድ ስምምነትን ለማሻሳል እየሰሩ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG