በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ - ዩ ኤስ ጂ ኤም’ የሚመሩ እጩ አቀረቡ 


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ - ዩ ኤስ ጂ ኤም’ ሎጎ በአሜሪካ ድምፅ ህንጻ ውስጥ፤ ዋሽንግተን ዲሲ፤ ኅዳር 22/2019
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ - ዩ ኤስ ጂ ኤም’ ሎጎ በአሜሪካ ድምፅ ህንጻ ውስጥ፤ ዋሽንግተን ዲሲ፤ ኅዳር 22/2019

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ድምጽን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በጀት የሚሰሩ አምስት ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን የሚቆጣጠረውን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ‘ዩናይትድ ስቴትስ ግሎባል ሚዲያ - ዩኤስጂኤም’ን እንዲመሩ ወግ አጥባቂ ሃሳቦች አራማጅ እና ጸኅፊውን ኤል ብሬንት ቦዜል ሦስተኛ’ን እጩ አድርገው አቅርበዋል።

"የመገናኛ ብዙኃን ጥናትና ምርምር ማዕከል መሥራች እና ፕሬዝዳንት ሆነው ለ38 ዓመታት እንዳገለገሉት እንደ ብረንት የኅትመት፣ የቴሌቭዥን እና የኢንተርኔት ዘገባዎችን ምሕዳር ጥሩ አድርጎ የሚረዳ የለም" ሲሉ ትረምፕ ትላንት ‘ትሩዝ ሶሺያል’ በተሰኘው የማሕበራዊ ሚዲያ መድረካቸው ላይ አስፍረዋል።

‘ዩኤስጂኤም’ ከአሜሪካ ድምፅ በተጨማሪ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚያሰራጨውን ’ሚድልኢስት ብሮድካስቲንግ ኔትወርክስ’፣ ‘ራዲዮ ፍሪ ዩሮፕ/ ራዲዮ ሊበሪቲ’፣ ‘ራዲዮ ፍሪ ኤዥያ’ እና ‘ኪዩባ ብሮድካስቲንግ ቢሮ’ የተባሉትን የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ይቆጣጠራል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG