በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ከአሁን ወዲያ ከሰሜን ኮርያ የሚደቀን የኑክሌር አደጋ የለም" - ፕሬዚዳንት ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “ከአሁን ወዲያ ከሰሜን ኮርያ የሚደቀን የኑክሌር አደጋ የለም” ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ጋር ሲንጋፖር ላይ ተነጋገረው ከተመለሱ በኋላ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “ከአሁን ወዲያ ከሰሜን ኮርያ የሚደቀን የኑክሌር አደጋ የለም” ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ጋር ሲንጋፖር ላይ ተነጋገረው ከተመለሱ በኋላ ነው።

“ከረዥም ጉዞ በኋላ ዛሬ ገባሁ። ነገር ግን ስልጣን ከያዝኩባት ቀን ይልቅ ሰው ሁሉ በአሁኑ ወቅት ደኅንነት እንዲሰማው ይገባል” የሚል መልዕክት በትዊተር አስተላልፈዋል። ከኪም ዦንግ ኡን ጋር ያደረኩት ስብሰባ ጥሩና አዎንታዊ ተመክሮ ነበር። ሰሜን ኮርያ ለወደፊቱ ትልቅ መሰረት አላት” ሲሉም አክለዋል።

የሰሜን ኮርያው መሪ “የኮርያ ልሳነ ምድር ከኑክሌር መሳርያ ነፃ እንድትሆን” በትላንቱ ስብሰባ ተስማምተዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ከደቡብ ኮርያ ጋር የሚደረገውን ወታደራዊ ልምምድ እንደሚያቆሙ ባልተጠበቃ ሁኔታ ተናግረዋል።

ትረምፕ አያይዘውም “ሁለታችንም ወገኖች በጥሩ መንፍስ እየተደራደርን ነው። ይህ እስከሆነ ድረስ ደግሞ የጦርነት ልምምዱን በማቆም ብዙ ገንዘብ ከብክነት እናድናለን” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG