በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪያቸውን ሊቀይሩ ነው


ፎቶ ፋይል፡- ጃን ቦልተን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪያቸውን ሊቀይሩ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪያቸውን ሊቀይሩ ነው። ፕሬዚዳንቱ አስተዳደሩን ከተረከቡ ባለፈው የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ጊዜ ብዛት ያላቸው ከፍተኛ የአስተዳደሩ ባለሥልጣናት ተሰናብተዋል።

የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪው የጦር ሠራዊት ጀነራል H R McMastern ቀድሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት ጃን ቦልተን እንደሚተኳቸው ሚስተር ትረምፕ ትናንት ሃሙስ ማታ በትዊተር አስታውቀዋል። ቦልተን በአሁኑ ወቅት በወግ አጥባቂው ፎክስ ቴሌቨዥን ጣቢያ ተንታኝ ናቸው።

አንድ የዋይት ኃውስ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ጄነራል ሜክማስተር ሥራቸውን ለቀው በጡረታ እንዲገለሉ ሚስተር ትረምፕ ተስማምተውበት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG