በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ውድዋርድ የቅጂ መብት ጥሷል ሲሉ ከሰሱ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋዜጠኛው ቦብ ውድዋርድ “ሬጅ” ለሚለው መጽሀፉ የተጠቀመበትን የቃለ መጠይቃቸውን ቅጂ በድምጽ ለማሳተም ምንም ዓይነት ፈቃድ አላገኝም ሲሉ ክስ መመስረታቸው ተሰምቷል፡፡

በፍሎሪዳ ግዛት ፔንሶኮላ ውስጥ በሚገኘው የፌዴራሉ ፍርድ ቤት የቀረበውና በጋዜጠኛው ውድዋርድ፣ አሳታሚው ሳይመን እንድ ሹስተር ኢንክ እና የአስታሚው እናት ድርጅት ፓራማውንት ግሎባል ላይ የተመሰረተው ክስ የ50 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቁ ተመልክቷል፡፡

አሳታሚውና ጋዜጠኛው ውድዋርድ በጋራ ባወጡት መግለጫ የትረምፕ ክስ ምንም መሰረት የሌለው መሆኑን ገልጸው በከፍተኛ ደረጃ እንደሚከላከሉት አስታውቀዋል፡፡

ትረምፕ በመሰረቱት ክስ ላይ ፈቃዳቸውን የገለጹት በውድዋርድ መጽሀፍ ላይ እንዲካተቱ እኤአ ከታህሳስ 2019 እስከ ነሀሴ 2020 ድረስ የተደረጉትን ቃለ መጠይቆች ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ሬጅ እኤአ በ2021 የታተመ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ እኤአ በ2022 የትረምፕ ቴፖች ተብለው በህዳር ወር በድምጽ የተለቀቁትን 20 የትረምፕ ቃለመጠይቆች በሚመለከት ውድዋርድና አሳታሚው ሳይመን እና ሹስተር የቅጂ መብቴን ጥሰዋል በሚል መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የቅጂ መብቱ ክስ የመጣው በፍሎሪዳ ዌስት ፓልም ቢች የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ እኤአ በ2016 ተቃናቃኛቸው በነበሩት ሂለሪ ክሊንተንና ሌሎች ላይ የሀሰት ክስ መስርተዋል በሚል ትረምፕ እና አንደኛው ጠበቃቸው ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንዲከፍሉ ከወሰኑባቸው ሳምንታት በኋላ መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG