በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሲንጋፖር

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሲንጋፖር ውስጥ ያካሄዱት ታሪካዊ ጉባዔ ተስፋ ሰጪ መሆኑን፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መሪዎች እየገለፁ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሲንጋፖር ውስጥ ያካሄዱት ታሪካዊ ጉባዔ ተስፋ ሰጪ መሆኑን፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መሪዎች እየገለፁ ናቸው።

የደቡብ ኮሪያው መሪ ሙን ጄ ኢን ያካሄዱት ዲፕሎማስያዊ ጥረት፣ ለሲንጋፖሩ የዩናይትድ ስቴትስና የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ግንኙነት ጥርጊያውን እንዳመቻቸም ይነገራል። እናም፣ «ሌሊቱን ባይኔ እንቅልፍ አልዞረም» የሚሉት ሙን ጄ ኢን፣ «የሁለቱ ጉባዔ፣ በኮሪያው ባሕረ-ገብ መሬት ሰላምንና ከኑክሊየር ነፃ የሆነ ቀጣና እንደሚፈጥር ተስፋቸውን ገልፀዋል።

ቤይጂንግ ውስጥ፣ ውጩ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣ የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት፣ የኮሪያውን ጦርነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዕልባት የሚሰጥ ሥምምነት እንደሚያስገኝ፣ ቻይና በፅኑ ታምናለች ብለዋል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ በጉብኝት ላይ ከሚገኙት ከማሌዥያው መሪ ማሃቲር ሞሐመድ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ የሁለቱ ሥምምነት ትክክለኛውን አቅጣጫ ከያዘ፣ ሰሜን ኮሪያ ብሩህ ተስፋ ይኖራታል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG