በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የኢራንን ውል እንደማያድሱ አስታወቁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተገባውን የኒኩሌር መርኃግብር ውል እንደማያድሱ አስታወቁ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተገባውን የኒኩሌር መርኃግብር ውል እንደማያድሱ አስታወቁ።

ቴህራን በስምምነቱ መሠረት ልትፈፅም የሚገቧቸውን ግዴታዎቿን እየተወጣች ስለመሆኑ ትረምፕ ይንፈጉ እንጂ ውሉን ሙሉ በሙሉ አልሠረዙትም።

በኢራን ላይ አዲስና የጠበቀ አካሄድ እንዲወሰድ ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል።

“ፍፃሜው የባሰ ሁከት መፍጠር፣ የባሰ ሽብርና የኢራን የኒኩሌር ጦር መሣሪያ ባለቤትነት የባሰ ሥጋት ወደሚሆንበት መጨረሻ እንደሚወስድ ቀድሞ መተንበይ የሚቻልበት ስምምነት እንዲቀጥል የሚያደርግ ማረጋገጫ ከእንግዲህ አልሰጥም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

አዲሱ ስልት “የኢራንን መረጋጋት እንዳይኖር የሚያደርግ እንቅስቃሴና በአካባቢው የእጅ አዙር የሽብር ቡድኖችን የመደገፍ አካሄድ” ለመቀልበስ ከዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ጋር መተባበርን የሚያካትት ነው ብለዋል ሚስተር ትረምፕ።

በተጨማሪም ኢራን ለሽብር ፈጠራ ጉዳይ ትሰጠዋለች ያሉትን የገንዘብ ድጋፍ ለመቆጣጠር እና የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢን ሥጋት ላይ የሚጥል የጦር መሣሪያዎች ግንባታዋን ለማስቆም ተጨማሪ ማዕቀቦችን መጣል እንደሚያስልግ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ከኢራን የዛሬ ሁለት ዓመት ስምምነት ላይ የደረሱትና ውልም የፈረሙት አምስቱ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባላትና ጀርመን የነበሩ ሲሆን የዛሬው የፕሬዚዳንት ትረምፕ አቋም ለጊዜው ውሉን ሙሉ በሙሉ የሚሠርዝ ሳይሆን የተወካዮች ምክር ቤቱ ኢራን በውሉ መሠረት ተነስተውላት የነበሩ ማዕቀቦችን መልሶ እንዲጥል የስድሣ ቀናት ጊዜ የሚሰጥ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG