በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ከኢራን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ትላንት ሰኞ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ትላንት ሰኞ ተናግረዋል።

ከኢጣልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባዔ ከኢራን ፕረዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ጋር ተገናኝተው የመነጋገር ፍላጎት ይኖራቸው እንዳሆነ በአንድ ጋዜጠኛ ሲጠየቁ "ተገናኝቶ በመነጋገር አምናለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“በተለይም ጦርነት ሊካሄድ በሚችልበት ጉዳይ፣ ስለሞት፣ ስለረሀብና ስለሌሎች ነገሮች ሲሆን ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ መነጋገሩ አይጎዳም” ብለዋል ፕረዚዳንት ትረምፕ።

ከኢራን ጋር ለመነጋገር ቅድመ-ግዴታ ያስቀምጡ እንደሆነ ሲጠየቁ፣ "ቅድመ ግዴታ አይኖርም። ለመነጋገር የሚፈልጉ ከሆነ አደርገዋለሁ" ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG