በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተወሰነ


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በአውሮፓው የቀን አቆጣጠር በ2016ቱ የምርጫ ዘመቻ ወቅት ፤ የወሲብ ፊልም ተዋናይቷን ስቶርሚ ዳንኤልን ዝም ለማሰኘት ገንዘብ ከፍለዋታል በሚል እንዲከሰሱ በኒው ዮርክ ከሕዝብ የተወጣጡ ዳኞች (ግራንድ ጁሪ) ትናንት ሐሙስ ወሰኑ፡፡

በወንጀል በመከሰስ ዶናልድ ትረምፕ የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡፡

ትረምፕ የጥፋተኝነት ውሳኔ ባይሰጣቸውም ሁለት ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ከሥልጣን እስከማስነሳት የሚችል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል ፡፡

በ2020ው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሸነፉት ዶናልድ ትረምፕ ይህ የክስ ውሳኔ የመጣባቸው በመጭው የ2024ቱ ምርጫ ተወዳድረው እንደገና ኋይት ሐውስ ቤተመንግሥት ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ባሉበት በዚህ ወቅት ነው፡፡

የኒው ዮርኩ የክስ ዝርዝር ይፋ ባለመደረጉ በምን ያህል የወንጀል ክሶች ሊከሰሱ እንደሚችሉ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም፡፡ የአሜሪካው የዜና ማሰራጫ ቴሌቭዥን ሲኤንኤን ፤ ትረምፕ ከ30 በላይ ክሶች የተመሰረቱባቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡

የትናንቱ ከሕዝብ የተውጣጡት ዳኞች ውሳኔው በዋሽንግተን ከፍተኛ ንግግርና ክርክር ቀስቅሷል፡፡ በውሳኔ የተቆጡ ሪፐብሊካኖች ዴሞክራቶችን "ለፖለቲካ መሳሪያነት እየተጠቀሙበት ነው" ሲሉ ዴሞክራቶች በበኩላቸው "ማንም ከሕግ በላይ ስላልሆነ ትረምፕም መከሰስ አለባቸው" እያሉ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG