በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምክር ቤቱ ውሳኔ ትራምፕና የወደፊቱ የፖለቲካ


የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምክር ቤቱ ከተመሰረተባቸው የፖለቲካ ክስ ነጻ ቢወጡም የወደፊቱ ፖለቲካ እጣቸው አጠራጣሪ ነው
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምክር ቤቱ ከተመሰረተባቸው የፖለቲካ ክስ ነጻ ቢወጡም የወደፊቱ ፖለቲካ እጣቸው አጠራጣሪ ነው

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በምክር ቤቱ ከተመሰረተባቸው የፖለቲካ ክስ ነጻ ቢወጡም የወደፊቱ ፖለቲካ እጣቸው አጠራጣሪ እንደሆነ ይቆያል፡፡

ምንም እንኳ የጥፋተኝነት ውሳኔውን ለማሳለፍ የጎደለው ድምጽ ጥቂት ቢሆንም፣ ከሚያስፈልጉ 67 ድምጾች፣ 57 የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት፣ ትራምፕ ጥፋተኛ ናቸው ሲሉ ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከዚያ ውስጥ ሰባቱ የራሳቸው ወገን የሆኑ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡

ከትራምፕ አስተዳደር ቀጥሎ ሪፐብሊካንኖች እና ዴሞክራቶች የሚገጥሟቸው ፈተናዎች የተለያዩ እንደሆነም ይነገራል፡፡

ትራምፕ እኤአ ጥር 6 ጆ ባይደን "ምርጫውን ሰርቀውታል" በሚለው የሀሰት ክስ ደጋፊዎቻቸውን በማነሳሳት በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ የአመጽ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል በሚል ከተከሰሱበት የፖለቲካ ክስ ጥፋተኛ አይደሉም ቢባሉም ዴሞክራቶቹ ግን የትራምፕ ጥፋትና ተጠያቂነት ግልጽ ነው ይላሉ፡፡

ሰባት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ከዴሞክራቶቹ ጋር ሲስማሙ፣ ሌሎች ሪፐብሊካኖች ግን በቂ ማስረጃ አልቀረበም ባይ ናቸው፡፡

የሮይተር እና ኤፕሶስ የህዝብ አስተያየት ድምጽ መሰብሰቢያ ውጤት እንደሚያሳየው፣ በዩናይትድ ስቴትስ 71 ከመቶ የሆኑ አዋቂዎችና ከዚያም ውስጥ ግማሾቹ ሪፐብሊካን በሆኑበት፣ ትራምፕ ለአመጹ በከፊል ጥፋተኛ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡

የትራምፕን መከሰስ ከሚደግፉ ሰዎች መካከል፣ ዛክ የተባሉት አሜሪካዊ ስለትራምፕ ጥፋት ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

“እሳቸው የሚያደርጉት ነገር ሁሉ በቋፍ ላይ ያለውን የምርጫ ሥርዓታችንን የበለጠ ማዳከም ነው”

"ምክር ቤቱ ጊዜውን የሚያጠፋው ዝም ብሎ ነው" የሚሉት ደግሞ የትራምፕ ደጋፊ የሆኑ ሼል ሬንሽ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ይህ እኮ ከሥልጣን እንዲነሱ የምትመሰረተው ክስ ነው፡፡ እሳቸው ግን ሥልጣናቸው ላይ አይደሉም፡፡”

ቅኝቶች እንደሚያሳዩት አብዛኞቹ ሪፐብሊካኖች ትራምፕን ይደግፋሉ፣ ከቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ ሚለር ሴንተር ባርባራ ፔሪ ይህንኑ ያረጋጣሉ፡፡

“በርግጥ 70 ከመቶ የሚሆኑት ሪፐብሊካኖች ጆ ባይደንን በህገወጥ መንገድ የተመረጡ ፕሬዚዳንት አድርገው ነው የሚያምኑት፡፡”

የሪፐብሊካን መሪዎች የተቀበሉት አንድ የሀሰት ነገር አለ፡፡ ይሁን እንጂ ተንታኞች እንደሚሉት የትራምፕ ደጋፊዎች የሚፈልጓቸውን ፖሊሲዎች አግኝተዋል፡፡ ከቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ ባርባራ ፔሪ ይህን ያስረዳሉ

“የቀረጥን ዋጋ ቀንሰዋል፡፡ የበዛውንም የመንግሥት ቁጥጥር በትንሹ እንዲኖር አድርገዋል፡፡ ወግ አጥባቂዎችን ከፍርድ ቤቶች ሰይመዋል፡፡ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ወግ አጥባቂዎች ዳኞችን አስመርጠዋል፡፡”

ከብሩኪንግ ተቋም ኢሌን ካምራክ፣ ትራምፕ በውጭው ፖሊሲ እና በድንበር ጉዳዮች የከረሩና ጠንካራ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ "ፕሬዚዳንት ባይደንና ምክር ቤቶቹን የተቆጣጠሩት ዴሞክራቶች ግን ከፊታቸው ብርቱ ፈተና ይጠብቃቸዋል ይላሉ፡፡" እንዲህ ገልጸውታል

“ዴሞክራቶቹ ከኮቪድ ሊያወጡን እና ኢኮኖሚውንም በቦታው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ በቀጥታ ሊሰሩ የሚገቧቸው ሥራዎች አሏቸው፡፡ በፓርቲው ውስጥ የፈለገው ዓይነት የርዕዮተ ዓለም ክፍፍል ቢኖር እንኳ ከሪፐብሊካኖች ጋር ሲስተያዩ ያላቸው ምርጫ፣ ቀጥ ብለው መስራት ብቻ ነው፡፡”

ትራምፕ በደጋፊዎቻቸው የተወደዱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዶቹ ሪፐብሊካኖች የሚነቅፏቸው ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ይታገሷቸዋል፡፡

በዚህ የተነሳ የብሩኪንክ ተቋም ምሁሯ ካምራክ እና ሌሎቹ ጓደኞቻቸው ትራምፕ ለወደፊቱ የተለያዩ እድሎች እንደሚጠብቋቸው ይገምታሉ፡፡ እንዲህ ይላሉ ካምራክ

“የሪፐብሊካን ፓርቲን ከመመራትና በ2024 በድጋሚ ፕሬዚዳንት ሆኖ ከመመረጥ አንስቶ ወደ እስር ቤት መወረድ ወይም አገር ለቆ ወደ ሩሲያ ወይም ሳኡዲ አረቢያ መሸሽ...ብቻ እንደዚያ ዓይነት እጣ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡”

የምክር ቤት አባላት ያልተስማሙባቸው ትራምፕ ግን ለወደፊቱ ብዙ ነገር ይጠብቃቸዋል፡፡ ትራምፕ አሁንም በርካታዎቹን የንግድ ጥቅሞቻቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ኢላማ ላደረጉት ጠበቆች የተጋለጡ ናቸው፡፡

ካምራክ እንደሚሉት ከአንድ ፕሬዚዳንት የሚጠበቀውን ነገር ሁሉ ላለማሟላት እንቢተኛ የሆነ ፕሬዚዳንት ማየት እንዳልተለመደ ሁሉ፣ ምናልባትም ያልተመደ የቀድሞ ፕሬዚዳንት መሆኑም የማይቀር ነገር ሊሆን ይችላል፡፡

የቪኦኤ ዘጋቢ ማይክ ኦስሊቪያን ካዘጋጀው ዘገባ፣ የተወሰደ፡፡

የምክር ቤቱ ውሳኔ ትራምፕና የወደፊቱ የፖለቲካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:17 0:00

XS
SM
MD
LG