በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶናልድ ትረምፕ ክስ ሂደት ቀጥሏል


አመጽ ቀስቅሰዋል ተብለው በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ክስ የቀረበባቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠበቆች የክስ መከላከያችንን ለማቅረብ አንድ ቀን ብቻ ይበቃናል አሉ።

የትረምፕ ጠበቆች ክሱን ለማድመጥ ችሎት በተቀመጡት የመወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ፊት ዛሬ ቀርበው ክሱን ሲከላከሉ አንድም የደንበኛቸውን የምስክርነት ቃል አያሰሙም። የቀድሞው ፕሬዚደንቱ በክሱ ሂደት ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ ዲሞክራት የክሱ አቅራቢዎች የክሳቸውን ጭብጥ አሰምተው ትናንት አጠናቅቀዋል።

ክሱን የሚመሩት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የትረምፕ ደጋፊዎች እኤአ ጥር 6 በምክር ቤቱ ህንጻ ስላካሄዱት አመጽ፣ ከዚህ በፊት ታይተው የማያውቁ የቪዲዮ ምስሎችን በማስረጃነት በማቅረብ የጆ ባይደንን አሸናፊነት የሚያረጋግጠውን የምርጫ ውጤትና ሂደት ለመቀልበስ ለተካሄደው አመጽ፣ ትረምፕ በቀጥታ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG