በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱ ትራምፕ በአመጹ ውስጥ የነበራቸውን ድርሻ እየመረመረ ነው


የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ የኒዮርኩክ ዴሞክራት ቻክ ሹመር ከሱን ከመሰረቱት የዴሞክራቲክ ህግ አውጭ አባላት ጋር በምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ
የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ የኒዮርኩክ ዴሞክራት ቻክ ሹመር ከሱን ከመሰረቱት የዴሞክራቲክ ህግ አውጭ አባላት ጋር በምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ

በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተመሰረተው ሁለተኛው ታሪካዊ ክስ በትናንትናው እለት በህግ መወሰኛው ምክር ቤት መደመጥ ጀምሯል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት፣ ትራምፕ ከወር በፊት በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ በደጋፊዎቻቸው የተካሄደውን አመጽ አነሳስተው እንደሆነ በመመርመር የጥፋተኝነት ውሳኔ መወሰን ይኖርባቸዋል፡፡

አመጹ የተካሄደው፣ የምክር ቤቱ አባላት በ2020ው ምርጫ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ድል የነሱትን፣ የጆባ ይደንን የምርጫ ውጤት፣ በማጽደቅ ሂደት ላይ እያሉ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ባለፈው ወር በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ የተካሄደውና የሰዎች ህይወት የጠፋበት አመጽ፣ በአሜሪካ የመጀመሪያው የሆነው ታሪካዊ ክስ እንዲመሰረት ምክንያት ሆኗል፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በዩናይትድ ስቴትስ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት የተከሰሱት ይህን አመጽና ሁከት አነሳስተዋል በሚል ነው፡፡

ትራምፕ በ2020ው ምርጫ ያሸንፉ መሆናቸውን በሀሰት ከተናገሩ በኋላ፣ ከየክፍለ ግዛቱ የተወጣጡ ተወካዮች ለጆ ባይደን የሰጡትን ያሸናፊነት ድምጽ ውጤት እንዳይቀበሉ ደጋፊዎቻቸውን በማነሳሳት ተከሰዋል፡፡ የመወሰኛም ምክር ቤት መሪ ሴነተር ቻክ ሹመር እንዲህ ይላሉ

“በአሜሪካ ታሪክ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ላይ የተመሰረተ የመጀመሪያው አሳፋሪ ክስ ነው”

እ.ኤ.አ ጥሪ 6 ከተካሄደው አመጽ ጋር ተያይዞ፣ ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ ሰዎች ተከሰዋል፡፡ ይህ የሆነው የምክር ቤት አባላት፣ ሁኔታው ለአገር ውስጥ ጽንፈኝነትና ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም ሊያስከትል ይችላል በማለት እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡

በፕሬዚዳንቱ ላይ የተመሰረተውንና በመታየት ላይ ያለውን ክስ የሚመሩት ዴሞክራቱ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ጄሚ ራስኪን እንዲህ ገልጸውታል

“ይህ የወደፊቷ አሜሪካ ገጽታ መሆን የለበትም፡፡ የህዝብን ፍላጎትና ድምጽ መቀበል ስላልፈለጉ ብቻ፣ እየተነሱ በመንግሥትና በተቋሞቻችን ላይ አመጽና ሁከት የሚያነሳሱ ፕሬዚዳንቶች ሊኖሩን አይገባም፡፡”

የአሜሪካ ብርሄራዊ ዘብ፣ አመጹ ከተካሄደበት ጥር 6 አንስቶ እስከ መጋቢት አጋማሽ ድረስ ብቻ፣ የምክር ቤቱን ህንጻ ደህንነት ለመጠበቅ ከሚያስፈልገው ገንዘብ በተጨማሪ፣ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ወጭ ያደርጋል፡፡

የምክር ቤቱ ችሎት በተጀመረበት የማክሰኞው ውሎ፣ ዴሞክራቶቹ ትራምፕ ጥፋተኛ መሆናቸውን የሚያሳዩ መከራከሪያዎቻቸውን አስደምጠዋል፡፡

ዴሞክራቱ የምክር ቤት አባል ዴቪድ ሲሲሊኒ ይህን ብለዋል

“ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በምክር ቤቱ ላይ የተፈጸመውን የአመጽ ጥቃት ሰለማነሳሳታቸው፣ በተናጥልና በቀጥታ ተጠያቂ መሆናቸውን የሚያሳይ፣ ከበቂ በላይ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ እናረጋግጣለን፡፡”

የዴሞክራቱ የምክር ቤት አባል ጆ ንጉሥ በበኩላቸው፣ ምንም እንኳ ትራምፕ አሁን በፕሬዚደንትነት ሥልጣናቸው ላይ ያሉ ባይሆንም፣ በሠሩት ሥራ ግን ተጠያቂ መሆን ይገባቸዋል በማለት ተከራክረዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል ጆ ንጉሥ

“ፕሬዚዳንቱ በመጨረሻ የሥልጣን ዘመናቸው የግልበጣ አመጽ አነሳስተው ምንም እንዳልተደረገ ነገር ዝም ብለው መሄድ አይኖርባቸውም፡፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲተላለፍ ቢያንስ ሁለት ሶስተኛው የምክር ቤት አባላት ድምጽ ያስፈልጋል፡፡ 50 ዴሞክራቶች ሊወስኑ ይችላሉ እንኳ ተብሎ ቢታሰብ ከሪፐብሊካኖቹ ቢያንስ 17ቱ ትራምፕ ጥፋተኛ ናቸው ብለው አብሮ መወሰን ይኖርባቸዋል፡፡

ትራምፕ ጥፋተኛ መሆናቸው ከተወሰነባቸው፣ የምክር ቤቱ አባላት እንደገና ተሰብስበው፣ ትራምፕ ካሁን በኋላ ከየትኛውም የመንግስት መዋቅር ውስጥም ሆነ የመንግሥት ኃላፊነት ተመልሰው እንዳይወዳደሩና እንዲታገዱ መወሰን ይኖርባቸዋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው መጀመሪያዉኑም ክሱን ለመመስረት የተፈለገው ለዚሁ ዓላማ ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡

የፕሬዚዳንቱ ጠበቆች ከሚመሩት መካከል ዴቪድ ሾን እንዲህ ያስረዳሉ

“ ብዙዎቹ የተከበሩ አሜሪካውያን እዚህ እየሆነ ያለውን ነገር ልክ እንደሆነው አድርገው ነው የሚያዩት፣ የፖለቲካ ወገንተኝነት ያላቸው ቡድኖች ዶናልድ ትራፕምን ከአሜሪካ ፖለቲካ ማራቅ ነው የሚፈልጉት፡፡ የእሳቸውን የአሜሪካ ራዕይ ከሚጋሩትና ከ74 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑ አሜሪካውያን መራጮች መነጠል ነው የሚፈልጉት፡፡”

እስከ እሁድ ድረስ ሊቀጥል ይችላል የተባለው ችሎቱ፣ ዛሬ ረቡዕም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች የራሳቸውን መከራከሪያዎቻቸውን ማስረጃዎቻቸውን ለማቅረብ 16 ሰዐታት አሏቸው፡፡

በምክር ቤቱ የቪኦኤ ዘጋቢ ካትሪን ጊፕሰን ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ምክር ቤቱ ትራምፕ በአመጹ ውስጥ የነበራቸውን ድርሻ እየመረመረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00


XS
SM
MD
LG