በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋይት ኃውስ የብሄራዊ ፀጥታ ክፍል የሚሰሩ ወታደራዊ መኮንን ቃላቸውን ሰጡ


ሌተናንት ኮሎኔል አለክሳንደር ቫይንድማን
ሌተናንት ኮሎኔል አለክሳንደር ቫይንድማን

በዋይት ኃውስ የብሄራዊ ፀጥታ ክፍል የሚሰሩ ወታደራዊ መኮንን ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት መርማሪዎች ቃላቸውን እያሰጡ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ ኡክራይን በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ላይ ምርመር እንድታካሄድ መጠየቃቸው እጅግ ስላሳሰባቸው ለኃላፊዎቻቸው ተናግረው እንዳነበር አብራርተዋል። ምርመራው የሚካሄደው ፕረዚዳንት ትረምፕ ሊያስከስሳቸው የሚችል በደል ፈፅመው ከሆነ ለማጣራት መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ሌተናንት ኮሎኔል አለክሳንደር ቫይንድማን ፕረዚዳንት ትረምፕ ከኡክራይኑ አቻቸው ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በስልክ ሲናጋገሩ ይሰሙ እንዳነበር በጽሁፍ ባቀረቡት ቃለ-ምስክርነት ገልጸዋል። “የስልኩ ጥሩ አሳስቦኛል። አንድ የውጭ መንግሥት በአሜሪካ ዜጋ ላይ ምርመራ እንዲያካሄድ መጠየቅ ተገቢ መስሎ አልታየኝም። ዩናይትድ ስቴትስ ኡክራይንን በምትደግፍበት ምክንያት ላይ ሊኖር የሚችል አመለካከት አሳስቦኛል” ሲሉ ለመርማሪዎቹ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ኡክራይን በምርጫ ተወዳዳርያቸው ባይደንና ልጃቸው ሀንተር ላይ ምርመር እንድታካሄድ ትረምፕ ሲጠይቁ አሜሪካ ለኡክራይን የመደበችውን $391 ሚልዮን ዶላር ረድዔት እንዳይሰጥ አዘግይተዋል። ኡክራይን ገንዘቡ ያስፈለጋት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል መገንጣል የሚፈልጉ ሩስያውን ጋር ለምታካሄደው ውጊያ ነው ተብሏል።

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጭ ዘመቻ የፋይናንስ ህግ መሰረት የውጭ እርዳታና መዋጮ መጠየቅ ህገ-ወጥ ተግባር ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG