ዋሺንግተን ዲሲ —
ትረምፕ ሥልጣናቸውን ከፖለቲካ አንፃር የራሳቸውን ጥቅም ለመጥበቅ ተጠቅመውበት እንደሆነ ለማወቅ በሚደረገው ምርመራ ወሳኝ ቦታ ያላቸው የምክር ቤት አባላት ተጻራሪ አመለካከቶችን አንፀባርቀዋል።
ዲሞክርስቶች ፕረዚዳንት ትረምፕ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚመሩት የተወካዮች ምክር ቤት የሥለላ ክፍል ኮሚቴ ሊቀመንበር አዳም ሼፍ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፕረዚዳንት ትረምፕ ዋናው ዲሞክራት የምርጫ ተወዳዳርያቸው በሆኑት ጆ ባይደን ላይ ኡክራይን ምርመር እንድትጀምር ጫና አድርገዋል ብለዋል። ኡክራይን በምስራቅ ክፍል ያሉትን የሩስያ ደጋፊ ተገንጣዮች የሚባሉትን ኃይሎች ለመዋጋት የሚያስፈልጋት $391 ሚልዮን ዶላር እንዲሰጣት ከመፍቀዳቸው በፊት ምርመራውን እንድትጀምር ተጭነዋታል ብለዋል ሼፍ ባደረጉት ንግግር።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ