በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ከሥልጣን የመባረሩ ጉዳይ እኔን አያሳስበኝም" - ፕሬዘዳንት ትረምፕ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሮይተርስ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ “ከሥልጣን የመባረሩ ጉዳይ እኔን አያሳስበኝም” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሮይተርስ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ “ከሥልጣን የመባረሩ ጉዳይ እኔን አያሳስበኝም” ብለዋል።

ፕሬዘዳንቱ ትላንት ከሮይተርስ ጋር ብቻ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ተንተርሦ የቀረበ ጽሑፍ -“አንድን ምንም ሥህተት ያልፈፀመና በሃገሪቱ ታሪክ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት የፈጠረን ሰው ከሥልጣን ማባረር ከባድ ነው” ማለታቸው ተጠቅሷል።

ተቃዋሚ ዲሞክራቶች ጉዳዩን ያነሱት፤ ሚስተር ትረምፕ ከ2016ቱ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በፊት በነገረ ፈጅ በማይክል ኮኸን አማካይነት ለሁለት ሴቶች ክፍያ ከመፈፀማቸው ጋር በተያያዘ ነው።

የፌዴራሉ ዓቃብያነ ሕግ ክፍያው የተፈጸመው በሚስተር ትረምፕ ትዕዛዝ ነው ብለዋል።

ዲሞክራቶች ለሴቶች በድብቅ የተከፈለው ገንዘብ መጠን ሕጉ ለምርጫ ዘመቻ መዋጮ ከሚፈቅደው በላይ እና በትረምፕ ዘመቻ አስተባባሪዎች በአግባቡ ያልተገለፀ ነው ይላሉ። ይህን መሰሉ የምርጫ ዘመቻን ሕግ የጣሰ አሠራር - ማንንም ከሥልጣኑ ሊያባርር የሚችል ወንጀል ነው ሲሉም የምክር ቤት አባላቱ ዲሞክራቶች ያስረዳሉ።

ትረምፕ ግን ክፍያዎቹ ለምርጫ ዘመቻ በመዋጮነት የተሰጡ ባለመሆናቸው፣ የፈፀምነው አንዳች ሥህተት የለም ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG