በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትራምፕ ክስ የካቲት መጀመሪያ በመወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ይታያል


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ያሳለፈውን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ የሚጠይቀውን ክስ ዛሬ በይፋ ወደ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሊልክ ነው። ምክር በቤቱ የወሰነው፤ ትራምፕ ለሥልጣን ሲሉ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ደጋፊዎቻቸው በምክር ቤቱ ላይ በደቦ የፈፀሙትን ጥቃት በማነሳሳት ወንጀል እንዲከሰሱ ነው። ትራምፕ ከየክፍለ ግዛቱ ተወካዮች የተገኘውን ድምፅና ኤሌክቶራል

ዴሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች ለዐቃቤ ሕግ እና ለትራምፕ ተከላካይ ጠበቆች የዝግጅት ጊዜ ለመስጠት እንዲቻ ጊዜው ትንሽም ቢሆን ቢዘገይ በሚለው ከተስማሙ በኋላ የክሱ ሂደት በሴኔት እንዲጀመር ለየካቲት 1/2013 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ቆርጠውለታል። ይህ ተጨማሪ ጊዜም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለካቢኔ አባልነት ያቀረቧቸውን እጩዎች ሴኔቱ እንዲያፀድቅ ዕድል ይሰጣቸዋል።

ትራምፕ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ለመባል የሴኔቱ ሁለት ሦስተኛ ድምፅ መስጠት አለበት። የሴኔቱ መቀመጫ እኩል ለእኩል በ50 ዴሞክራትና በ50 ሪፐብሊካን የተያዘ ሲሆን ዴሞክራቶች ሙሉ በሙሉ ትራምፕ ጥፋተኛና ናቸው ብለው ይወስናሉ ተብሎ ቢገመት ተጨማሪ 17 ሪፐብሊካኖች ድምፅ መስጠት ይኖርባቸዋል።

ትራምፕ በዚህ ክስ ጥፋተኛ ከተባሉም ከዚህ በኋላ የትኛውንም የፌደራል መንግሥት ሥልጣን እንዳይዙ ይደረጋሉ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ245 ዓመታት የአሜሪካ ታሪክ በልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ ብቸኛ ፕሬዚዳንት ናቸው።

XS
SM
MD
LG