በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትራምፕ ላይ የቀረበው ክስ ማጠቃለያ ተሰማ


በቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ በተመሰረተው ክስ በምክር ቤቱ በመታየት ላይ ባለው ችሎት በኤግዝቢትነት የቀረቡ መረጃዎች
በቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ በተመሰረተው ክስ በምክር ቤቱ በመታየት ላይ ባለው ችሎት በኤግዝቢትነት የቀረቡ መረጃዎች

በቀደሞ ፕሬዚዳንት ላይ የተመሠረተውን ክስ የሚመሩት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ትናንት ሀሙስ የክስ ክርክራቸውን ቋጭተዋል፡፡ ትራምፕ የጆ ባይደንን አሸናፊነት የሚያረጋግጠውን፣ የየክፍለ ግዛቶቹን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ፣ በተደረገው ሙከራ በቀጥታ ተጠያቂ ናቸው በማለት፣ ተከራክረዋል፡፡

እኤአ ጥር 6፣ በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ የተፈጸመውን የአመጽ ጥቃት አነሳስተዋል በሚል፣ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ የተመሰረተው ክስ ማጠቃለያ፣ በትናንትና እለት ተሰምቷል።

በትራምፕ ላይ የቀረበው ክስ ማጠቃለያ ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00


በክሱ ሂደት ላይ በኤግዝቢትነት ከቀረቡት የቪዲዮ ምስሎች መካክል“እዚህ የመጣነው በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጥያቄ ነው” የሚለው ይገኝበታል፡፡

በፕሬዚዳንቱ ላይ የተመሠረተውን ክስ የመሩት፣ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የመክፈቻ ክርክራቸውን፣ የትራምፕን እጣ ለሚወሰኑት የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት፣ ወይም ሴነተሮች፣ አሰምተው ጨርሰዋል፡፡

ክርክሩን ካሰሙት መካከል፣ ዴሞክራቱ ጃኩዊን ካስትሮ “ ጥር 6 ማለት አሜሪካ አለመሆንዋን ለዓለም ሁሉ እናሳይ” ብለዋል፡፡

ሌላዋ ዴሞክራት የምክር ቤት አባል ዳያና ደጌት በበኩላቸው እንዲህ ብለዋል

“በአመጹ የተሳተፉት ነውጠኞች፣ ለህግ አሰከባሪዎቹ፣ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ትዕዛዝ እየተከተሉ መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በሚሰሩት ወንጀል አላፈሩም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከጠቅላይ አዛዡ ትዕዛዝ እየተከተሉ መሆኑን ስላወቁ እንደማይቀጡ ተሰምቷቸዋል፡፡ግን ተሳስተዋል!”

ባለፈው ረቡዕ የታየው የቪዲዮ ምስል ጥልቅና ዝርዝር ነበር፡፡ የአገሪቱ ህግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላት ከነውጠኞቹ ጥቃት ሲሸሹ አሳይቷል፡፡

ትናንት ሀሙስ የተሰማው የከሳሾች ክርክርም፣ የቀደሞው ፕሬዚዳንት፣ ካሁን በኋላ በየትኛውም የመንግሥት ኃላፊነት እንዳይወዳደሩ ካልተደረገ ደጋፊዎቻቸውን ለተመሳሳይ ጥቃት ሊያነሳሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

ከተካራካሪዎቹ የምክር ቤት አባላት ዴሞክራቱ ቴድ ሊው እንዲህ ብለዋል

“ከአራት ዓመት በኋላ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተመልሰው ቢወዳደሩ አልፈራም፡፡ የምፈራው ተመልሰው ቢወዳደሩ እንደገና ይሸነፋሉ፡፡ እንደገና ሲሸነፉ ደግሞ ይህኑን መልሰው ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡”

ላለፉት ሁለት ቀና ዴሞክራቶቹ ትራምፕ አመጽን እንደገና ሊያበረታቱ ይችላሉ በማለት ተከራክረዋል፡፡ ምክንያቱም በ2020 በተደረገውን ምርጫ መሸነፋቸውን እስካሁንም ስላልተቀበሉ የአገሪቱ ዋና ከተማ አሁንም በጥበቃ ሥር ናት፡፡ ዴሞክራቱ ቴድ ሊው አሁንም ይቀጥላሉ

“ የወደፊቱን አመጽ ልታስቀር የምትችልውን ያቺን አንዲት ቃል እንኳ አይናገሩም፡፡ ምርጫው አልተሰረቀም! እስካሁን ያንን አላሉም፡፡ ያንን ባለማለታቸው ነው እስካሁን ድረስ ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ የብሄራዊ ዘብ ወታደሮች ከደጅ የቆሙት፡፡”

ትራምፕ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመስጠት፣ ከዴሞክራቶች ድምጽ ጋር፣ አስፈላጊ የሆኑትን፣ ቢያንስ የ17 የሪፐብካን ምክር ቤት አባላትን ድምጽ፣ የማግኘቱ ነገር ግን አሁንም አጠራጣሪ ይመስላል፡፡ ክሱን የሚመሩት ዴሞክራቱ ጃሚ ራስኪን ግን፣ ሪፐብሊካኖቹ ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ ውጤቱን ከግምት እንዲያስገቡ በመጠየቅ ይህን ብለዋል

“ ፕሬዚዳንት ትራምፕማ ያደረጉት ነገር ፍጹም ትክክል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ እንደገና ወደ ሥልጣን ቢመለሱ ይህ ነገር ይደገማል፡፡ ያን ጊዜ ራሳችንን እንጂ ማንንም መውቀስ አንችልም፡፡”

የትራምፕ ተከላካይ ጠበቆች ደግሞ፣ ዛሬ ዓርብ መከላከያቸውን ያሰማሉ፡፡ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ድርጊት አመጽ ስለማነሳሳት ከሚለው የህግ መተላለፍ ጋር አይገናኝም በማለት ይከራከራሉ፡፡

በምክር ቤቱ አባላት፣ በትራምፕ ክስ ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ድምጽ ወይም የመጨረሻ ውሳኔ፣ በሚቀጥለው ሳምንት መግቢያ ላይ፣ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

(በምክር ቤቱ የቪኦኤ ዘጋቢ፣ ካትሪን ጊፕሰን ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG